በመንግስት ተቋማት ወጥ፣ ተነባቢ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃና ተግባቦት እንዲሁም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አመራርና ሥርአት በመዘርጋት ለሁሉም ዜጎች የመንግስት መረጃን የማግኘት ዕድል በመፈጠር፤የመንግሥት አጀንዳዎች ተቀባይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ፤ የኮሙኒኬሽን ተግባራት በጠንካራ፣የምርምር፣ ሙያዊ ብቃትና ፈጠራ ማጎልበት፡፡
የዜጎችን መንግስታዊ የመረጃ ፍላጎት የሚያሟላ ተአማኒ፣ ውጤታማ እና ቀድሞ ተንባይ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት በ2022 እውን ማድረግ፤
1. ግልጽነትና ክፍት፣
2. ብዙኃንነትና እኩልነት፣
3. ተደራሽነት፣ወቅታዊነትና ምላሽ ሰጭነት፣
4. ሙያዊነትና ፈጠራ፣
5. ተኣማንነትና ትክክለኛነት፣
የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግልት ሥልጣንና ተግባራት ከሚሰጡት ሕጎች ዋነኛው የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቊጥር 1263/2014 ተከትሎ በወጣ በድንብ ቊጥር 488/2014 ሲኾን በማቋቋሚያ ደንቡ ከተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መካከል አራት ዓላማዎችና ሃያ ተግባርና ኃላፊነት እንደሚኖሩት ተደንግጓል።
አገልግሎቱ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በርካታ ዓላማዎችን እንደሚያሳካ የሚጠበቅ ኾኖ በዋናነት በሚከተሉት ዓላማዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ እነሱም፡-
1. በመንግሥት የመረጃና የተግባቦት ወይም ኮሙኒኬሽን ሥርአት የቃል አቀባይነትና ስትራቴጅካዊ የመሪነት ሚና መጫወት፤
2. መንግሥት ፖሊሲዎች፣ መርሐ ግብሮች፣ ፕሮግራሞችና ዕቅድችን መሠረት ያደረጉ አጀንዳዎችን በማዘጋጀት ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃና የተግባቦት ሥርአትን በመፍጠር ምልዓተ ሕዝቡን ተደራሽ ማድረግና ተሳትፎዉን ማሳደግ፤
3. በልዩ ልዩ መንግሥት ተቋማት፣ የሚዲያ አዉታሮችና በባለድርሻ አካላት መካከል ውጤታማና ቀልጣፋ የመረጃና የተግባቦት ሥርአትን በመፍጠር ኹሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ከመንግሥት መረጃ ዕኩል የሚያገኙበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር፤
4. መንግሥትን ፖሊሲዎች፣ መርሐ ግብሮችና ፕሮግራሞችን መሠረት በማድረግ ኅብረ- ብሔራዊ አንድነትን፣ የሀገር ፍቅርን፣ ሀገራዊ ተግባቦትን፣ የዳሞክራሲ ባህልን ለማጎልበትና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃና የተግባቦት ሥርአት ለመዘርጋት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አመራር መስጠትን ያካተተ ነው፡፡
ተቋሙ በደንብ ቊጥር 488/2014 ከተሰጡት ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ፡-
1. ከሕዝብ ሰላምና ደኅንነት፣ ከታላላቅ ሀገራዊ ክንዉኖች፣ ከተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች፣ ከዘመቻ ሥራዎች ወዘተ ጋር በተያያዘ በየደረጃዉ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ መተንተን፣ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረቱ አጀንዳዎችን መቅረጽ፣ ማሰራጨትና በመሠረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግባባትን መፍጠር፣
2. መንግሥት አጀንዳና አፈጻጸሞችን ተደራሽ የሚያደርጉ በጠንካራ አደረጃጀትና ኔትዎርኪንግ የተደገፈ የዲጂታል ሚዲያ አሠራር መዘርጋት፣
3. በሀገሪቱ እየተስፋፋ ባለዉ አካታች ሥርአት የተፈጠሩ መልካም እድሎች፣ በሀገራዊ ታሪካዊ ቅርሶችና ባህላዊ እሴቶች፣ የሀገሪቱን አህጉራዊና ቀጠናዊ ተሳትፎን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገነዘብ መርዳትና በጎ አመለካከትን ማዳበር፣
4. መንግሥት ፖሊሲዎችን፣ መርሐ ግብሮችን፣ አገልግሎቶችና አፈጻጸሞች እንዲሁም ዜጎችን በሀገራዊ ልማትና ዳሞክራሲ ሒደት ግንባታ ለማሳተፍ የሚያስችል የተቀናጀና የተናበበ የተግባቦት ሥራን ከፌዴራልና ከክልል የኮሙኒኬሽን ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት፣
5. የመንግሥትን ፖሊሲ፣ መርሕ እና ዕቅድ መሠረት በማድረግ ማኅበረሰብን ተደራሽ የሚያደርጉ አጀንዳዎችን ማዘጋጀት፤ እንዱሁም የማኅበረሰብን ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያሳድጉ ንቅናቄዎችን መፍጠር፤
6. በየጊዜው የሚፈጠሩ ሀገራዊ አጀንዳዎችንና ንቅናቄዎችን ውጤታማነት መገምገምና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ማሳወቅ፣
7. የመንግሥትን አጀንዳዎች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ኹሉንም ዓይነት የኢንፎርሜሽን ቴክኖልጂ ውጤቶችን በብቃት፣ በጥራትና በስፋት መጠቀም፤
8. የመንግሥትን ፖሊሲ፣ መርሕና ዕቅድ መሠረት በማድረግ፤ እንዲሁም ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን፣ ሀገራዊ ተግባቦትን፣ የዳሞክራሲ ባህል መጎልበትን፣ ሁለንተናዊ ብልጽግና መፍጠርንና የመሳሰሉትን መሠረት በሚያደርግ ማዕቀፍ ሚዲያዎችን መምራት፤
9. ለፌዳራል መንግሥት ተጠሪ በኾኑ መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት የሚገኙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችን ከየመሥሪያ ቤቶቹና ተቋማቱ የበላይ ኃላፊዎች ጋር በመመካከር መመደብ፣ መከታተልና ሥራቸውን መቆጣጠር፤ አቅማቸዉን መገንባት፣
10. ለመንግሥት ተጠሪ የአሥር መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት ለሚመድቡ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ለሥራቸው የሚኾን የአሠራር መርሕ፣ ደረጃና ሥርአት ማውጣትና ተግባራዊ እንዲደረግ ማስቻል፤
11. ለክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መሥሪያ ቤቶች የኹለትዮሽ የተግባቦት ሥራን ለማከናወን የሚያስችል አቅምን መገንባት፣
12. ከሕዝብ ሰላምና ደኅንነት፣ ከታላላቅ ሀገራዊ ክንውኖች፣ ከተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋ፣ ከዘመቻ ሥራዎች፣ ከግጭቶች እና ከመሳሰለት ጋር በተያያዘ በሚዲያ አዝማሚያዎች ዳሰሳና በሕዝብ አስተያየት ጥናቶች መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ በመተንተን፣ ድምዳሜዎችን ለባለድርሻ አካላት ማሳወቅና አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣
13. በተተነተኑ፣ በተደራጁና ይዘታቸዉ በታወቀ መረጃዎች ላይ በመመሥረት ጋዜጣዊ መግለጫዎችን፣ ጋዜጣዊ ጉባኤዎችንና ምላሾችን እንደአስፈሊጊነቱ ማዘጋጀት፤
14. የቅድመ ቀውስ ትንተና በመሥራት እንዲሁም ድንገት በሚፈጠሩ አደጋዎችና ግጭቶች ዙሪያ መረጃዎችን በፍጥነት በማሰባሰብና በማደራጀት ትክክለኛዉን መረጃ በፈጣን መንገድ ለባለድርሻ አካላትና ለዜጎች ማቅረብ፤
15. የመንግሥትን አጀንዳዎች ወደ ሕዝብ ለማስረጽ የሚረዳ የሙዚቃ፣ የፊልም፣ የቴአትር፣ የባህላዊ ክንውኖችና የመሳሰሉትን ዝግጅቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ማዘጋጀት ወይም ዝግጅቶችን መደገፍ፤
16. በብሔራዊ ጥቅም፣ የሀገር ሉዓላዊነት፣ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች፣ ሰላም፣ ደኅንነትና የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ከግል ሚዲያዎች ጋር ተቀራርቦ መሥራት፤
17. የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በመንግሥት ዋና ዋና የትኩረት አጃንዳና አፈጻጸም በሚወጣላቸው የይዘት መርሐ ግብር መሠረት ለሕዝብ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን እንዲሰጡ ማድረግ፤
18. በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ኢትዮጵያን በሚመለከት የሚወጡ የሚዲያ መረጃዎችን ዳሰሳ በመሥራት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያቀርባል፡፡ ከዳሰሳው መረጃዎች በመነሣትም አስፈሊጊዉን የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ይቀርጻል፣
19. በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የሀገር ሽማግላዎችን፣ ታዋቂ ሰዎችን፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ታዋቂ ነጋዴዎችን፣ ስፖርተኞችን፣ ማኅበራዊ አንቂዎችን እና የመሳሰሉትን በልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ መንገዶች በመመዝገብና መረብ በመዘርጋት (ኔትወርክ) ሀገራዊ መረጃዎች፣ ሐሳቦች፣ አጀንዳዎችና ሌሎችም እንዲደርሷቸው በማድረግ፣ በመንግሥት አጀንዳዎች ላይ መግባባት እንዲፈጠር ማድረግ፣
20. የተለያዩ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ፎረሞችን በማቋቋም እና ሌሎች የግንኙነት መድረኮችን በመፍጠር ወጥነት ያለው የተግባቦት ዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ሥርአት በመፍጠር የሀገሪቱን ገጽታ መገንባት፡፡