|

የፕሬስ መግለጫ

ኢትዮጵያ ነገዋን ዛሬ እየሠራች ነው! ነገ የሚወሰነው ዛሬ በምንሠራው ሥራ ነው! የነገ ስኬታችን የሚቀረጸው በዛሬው ጥረታችን ነው። ከትናንት መልካም ልምዶችን በመቅሰም፣ ዛሬን በትክክል አጢኖ የነገን ራዕይ ዛሬ ላይ ሆኖ መገንባት የመንግሥታችን ጽኑ እምነትና መለያ ባህሪ ነው። ሀገር በቀል ዕውቀትን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ ነገን ለመዋጀት መዘጋጀት ከዚህ ትውልድ የሚጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት እንደኾነ መንግሥት በፅኑ ያምናል፡፡…

|

የፕሬስ መግለጫ

ብዝኃነታችን የምንደምቅበት ጌጥ፣ የተደመረ ዐቅማችን ማሳያ ነው! ኢትዮጵያ የብዝኃ ማንነቶች ድምር ናት፡፡ ኢትዮጵያውያን ከሚኖሩበት የአየር ንብረት እስከ አመጋገባቸው፤ ከአመራረታቸው እስከ አለባበሳቸው፤ ከሃይማኖታቸው እስከ ፖለቲካዊ አመለካከታቸው በርካታ ብዝኃነቶች ያስጌጧቸዋል፡፡ የእነዚህ ብዝኃነቶች ድምር ደግሞ የኢትዮጵያ የማድረግ ዐቅም ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን ብዝኃነት ለዘመናት የማይታረቁ የልዩነትና ግጭት ምንጭ ተደርጎ እንዲታይ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ያለመታከት ሠርተዋል፡፡ በዚህም በየዘመኑ የታዩ ስኬታማ ድሎችን በአጭር…

|

የፕሬስ መግለጫ

እንኳን ለጳጉሜን 3 የፅናት ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን! ፅናት የኢትዮጵያውያን የትናንትም የዛሬም መገለጫ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያን የጋራ ዐጥንት እና ደም ተጠብቃ የቆየች የኩራት እና ክብር ምንጭ ናት፡፡ ለዚህም ነው ከትናንት እስከ ዛሬ ከየትኛዉም አቅጣጫ፣ በማንኛዉም ኃይል የሚቃጡ ጥቃቶችን ኹሉ በጀግንነት መመከት፣ ነፃ እና ሉዓላዊ ሀገር ለትውልድ ማስረከብ የተቻለው፡፡ ጳጒሜን 3 ቀንን የፅናት ቀን በሚል ስያሜ የምናከብረዉም…

|

መንግሥት ሌብነትን እና ሕገወጥነትን ለመከላከል ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው ፡፡

ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ እና የሀገር ሀብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታወቀ። የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፈጣን ልማትና ዕድገት እንድታረጋግጥ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰው፣ በዚህም…

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች!!

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ የዲሞክራሲ ሥርዓት ባለቤትነትን እና ለሰላም ያለውን ጽኑ ፍላጎት በተግባር ያረጋገጠበት ታሪካዊ ክስተት ነው። የምርጫው የሀገርና የሕዝብ የህልውና መሠረት መሆኑን መንግሥት በጽኑ የሚያምን በመሆኑ ፍትሐዊ፣ ተአማኒና ወቅቱን የጠበቀ እንዲሆን ከመንግሥትና ከሕዝብ ጋር በቅንጅት ሲሠራ ቆይቷል። የሀገሪቱን የለውጥ ጉዞ ለማደናቀፍ በውስጥ እና በውጭ ኃይሎች የተቀናጁ የጥፋት ሙከራዎች ተደርገዋል። መሠረተ ልማቶችን በማውደም እና…

ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ማለዳ ላይ፤ የመጀመሪያው የወገግታ ጭላንጭል በከፍታማዎቹ የኢትዮጵያ ተራሮች ላይ ፈንጥቆ ጨለማውን ሳይቀድ በፊት ኢትዮጵያውያን ረጃጅም ሰልፍ ተሰልፈዋል። በጅማ፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳ፣ በባሕር ዳር እንዲሁም ስማቸው በዓለም አቀፍ የዜና ጋዜጣዎች ላይ ፈጽሞ ሊወጣ በማይችሉ ከተሞችና መንደሮች ውስጥ ያሉ ወንዶችና ሴቶች፤ ወሳኝ ተግባር ለመፈጸም በሰልፍ ቆሙ። ድምፅ ሰጡ! ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከሃምሳ…

|

ኢትዮጵያ አዲሲቷ የተስፋ አድማስ ናት!

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ የታሪክ አውድ ውስጥ አዲስ ትርጉምና ጽኑ ቃል-ኪዳን ተላብሶ ብቅ ያለ፣ ለሀገራችንና ለሕዝቦቿም አዲስ የተስፋ አድማስን የፈነጠቀ ክስተት ነበር። ይህ ዕለት ኢትዮጵያን ተብትቦ ይዞ ከነበረው ውስብስብ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቅርቃር አውጥቶ ወደ ብሩህ መጻኢ ዕድል ለማሸጋገር የተገባ ታላቅ የትውልድ…

|

ፈተናን ወደ ዕድል የቀየረ የዲፕሎማሲ ከፍታ!

መጋቢት 22 /2018 ዓ.ም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት ስምንት ዓመታት የተከተለው ንቁና ስልታዊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ የሀገራችንን የውጭ ግንኙነት ለዘመናት በተዛባ መልኩ ይዞት ከነበረው “በጠላቶች የመከበብ እይታ” በማላቀቅ ለላቀ ዓለም አቀፋዊ ከፍታ የሚመጥን መሠረት ጥሏል። የለውጡ መንግሥት የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ዋነኛ መለኪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ነው። ሀገራችን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የራሷን የሉዓላዊነትና የልማት ፍላጎት ማዕከል…

|

አካታች ፖለቲካዊ ለውጦች ለጽኑ ሀገራዊ መሠረት

መጋቢት 21/2018 ዓ.ም የኢፌድሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የኢፌዴሪ መንግሥት ባለፉት የለውጥ ዓመታት አገራችንን ከነበረችበት ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ቀውስ አውጥቶ ወደ ተሟላ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር የነደፋቸውን ስልታዊ ግቦች በላቀ ጽናትና ስኬት ወደ ተግባር ቀይሯል። የዚህ ታሪካዊ ሽግግር ዋነኛ ስኬት ለዘመናት ኢትዮጵያን ሲንድ የነበረውን “የመሐል እና የዳር” አግላይ ፖለቲካዊ ትርክት በመስበር እያንዳንዱ ዜጋና እያንዳንዱ አካባቢ የሥልጣንና የሀብት…