የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት አካሒዷል

በመድረኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል ምላሸና ማብራሪያ የሰጡባቸው ጉዳዮች በአጭሩ እንደሚከተለው ተዘጋጀተዋል፡፡

ከለውጡ በኋላ የተደረገውን የሰላም ጥሪ  ለሁሉም የፖለቲካ  ታርቲዎች  ምንም አይነት ልዩነት ሳይኖር በተመሳሳይ መልኩ መደረጉን አንስተው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም በዲሞክራሲ እና በድርድር፤ በኃሳብ በመትጋት  እንጂ  በአፈ ሙዝ (በጠመንጃ) ስልጣ እንደማይያዝ በማብራራት፡፡

በአማራ ክልል በተደረገ ህዝባዊ ውይይት የልማት ጥያቄ፤ የህገ መንግስት ጥያቄ እና የወሰን ይገባኛ ጥያቄ  በዋናነት  መነሳታቸውን እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችም መነሳታቸውን  አንስተዋል፡፡

  1. ከመሰረተ ልማት አኳያ

ባለፉት 6 ዓመታት ብቻ በክልሉ 53 የመንገድ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው እየተሰሩ እንደሚገኙ እና እነዚህም 3200 ኪ.ሜ እንደምሸፍኑ ከነዚህም ውስጥ 1200ኪ.ሜ ተጠናቀው  ስራ መጀመሯቸውን  ይህ ደግሞ በክልሉ ያለውን መሰረተ ልማት ስራ የሚያፋጥን ስራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መንግስት በአፍሪካ ትልቁ የሚባል ድልድይ 2.4 ቢሊዮን ብር ወጭ አውጥቶ መገባንቱ፤ክልሉ ለቱሪስት ምቹ  እንዲሆን በጎርጎራ ላይ የሰራው ስራ  የህዝቡን የልማት ጥያቄ የሚመልስ መሆኑን፤

የላሊበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የፈረሳዩን ፕሬዝዳት ቦታው ድረስ በመጋበዝ   እድሳት እዲደረግለት የተሰራውን ስራ አንስተው፣ የፋሲል ቤተ መንግስት ግማሽ አካሉ ፈርሶ የነበረ መሆኑን እና በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ  ሙሉ ጥገና ለማድረግና  ለማደስ እየተደረገ የነበረው ጥረት በጦርነት ምክንያት አለመሳካቱን፤ የጣናን ውሃ እስከ ጎንደር የመውሰድ ስራም ተጀምሮ እንደነበር፤ በቱሪዝም በግብርና እና በኢንደስትሪው ዘርፍ  በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ያሉ ቢሆንም በጦርነቱ ምክያት  ማስቀጠል አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡

2.የህገ መንግስት ማሻሻያዎችን በተመለከተ

ትናንሽ የሚባሉ አጀንዳዎችን ላይ ስንጋጭ ስንጣላ ጊዜያችንን ከምናጠፋ  በውይይት በምክክር በሃሳብ ተግባብተን ከኛ የሚሻገር  ህገ መንግስት እንዲኖረን የሚያደርግ የምክክር ኮሚሽን መቋቋሙን በማንሳት  አብረን በመሆን ዘመን የሚሻገር  ህገ መንግስት ብናቋቋም የተሻለ እንደሚሆን አንስተዋል፡፡

  • የወሰን ይገባኛል ጠያቄዎችን በተመለከተ

ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ መንገድ መሆን አለበት ያሉ ሲሆን ይህም የሐገር ሽማግሌዎች በተሳተፉበት የህዝብ ውይይት እና ምክር ቢሆን ዘላቂ ሰላም  በህዝቦች መካከል ማረጋጋጥ እንደምንችል ገልጸው እስከዛ ድረስ ግን የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ፤ የአከባቢው ህዝቢችም ወደ ተስማማቸው ክልል ይቀላቀላሉ  ተብሎ ሲወሰን  ጦርነት አጋጥሞናል ብለዋል፡፡

የምንፈልገው ሰላም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ግጭት የሚያጎለው እንጂ የሚጨምረው ነገር እንደሌለው፤ችግሮችን  በሰላም ተነጋግሮ መፍታት እንደሚያስፈልግ ለዚህ ደግሞ የፌደራል መንግስት ዝግጁ መሆኑን  በአጽኖት አንስተዋል፡፡  

  • የትግራይ ድርድርን በተመለከተ

የኢትዮጵያ እና የትግራይን  ድርድር (የፕሪቶሪያውን ስምነት) የአፍሪካ ሕብረት አወያይ ስለነበረም ጭምር ስምነቱን ለአለም ፖስት ማድረጉን ይህ ደግሞ ድርድሩ ለአለም ግልጽ  መሆኑን አንስተው፤የትግራይ ጊዜአዊ መንግስት እና የፌድራል መንግስት በጋራ በመሆን ያስገኙዋቸው ድሎት መካከል፤

የክልልሉ የአየር መንገድ ስራዎች፤ ሰፋፊ የቴሌ ስራዎች፤ የባንክ እቅስቃሴዎች፤ በጤናው ዘርፍ  በስፋት የማስጀመር ስራ፤ ሁሉም የዩኒቨርሲቲዎች እና የትምህርት ተቋማት ትምህርት መጀመራቸውን በ ኢንዱስትሪው ዘርፍ 217 ፋብሪካዎች ስራ መጀመራቸውን፤ 630ሺ ሔክታር መሬት መታረሱን፤500 ትራክተሮች እና 300 ፓንፖች   ተገዝተው መንገድ ላይ መሆናቸውን፤100ሺ ኩንታል ማዳበርያ ወደ ክልሉ መላኩን አንስተዋል፡፡ ይህ ሁሉ በመንግሰት እየተደረገ ያለ ድጋፍ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባልም ብለዋል፡፡

ይህ በቂ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆኖም የኢትዮጵያን አቅም ውስንነት ሆኖ ነው እንጂ ከዚህ  በላይ እንደሚገባቸው አንስተዋል፡፡ በጣም በርካታ ድል ተገኝቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎደለውን ከጊዜያዊ  አስተዳደሩ ጋር እየተነጋገርን የምናሟላው ይሆናል ብለዋል፡፡

አርበኝነት ጦረኝነት መሆን የለበትም በልማት፤ በሰላም  በማስታረቅ አርበኛ መሆን ይቻላል ያሉ ሲሆን ፤ስልጣን በኃይል ብቻ እንደማይገኝ አንስተዋል፡፡ ለወጣቱ የስራ እድል ለመፍጠር  (ስራ አጥነትን ለመቀነስ ) በርካታ ስራዎችን እንደሚፈጠር፤ዲሞክራሲን መለማማድ እዳለብን ዲሞክራሲን በእሴት እና በባህል ግንባታ እጅግ  በህግ ብቻ እንደማይመጣ ገልጸዋል፡፡

ሕግ የማስከበር  ስራን አሁንም አጠናክረን እንቀጥላላን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለውይይት እና ለንግግር በራችን ክፍት ነው ብለዋል ፡፡

ኢትዮጵያ እስካሁን የነበረው አካሔድ ትተንበተሻለ መንገድ መሔድ  መምረጣችን፤ የሚዲያ አማራጭ መብዛቱ እና ለመረጃዎችና ለኑሮ እና ለዲሞክራሲ ምቹ ሁኔታዎች መብዛታቸው ጸብ እና ጥላቻ እንዲበዛ ምክንያት በሆኑን አነስተዋል፡፡

የጋራ ትርክትን በተመለከተ ለትላንት ስፋጅ ነገን እያጣን መሆኑን በጦርነት ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ የአፍሪካ ሃገራትን እንደ ምሳሌ በማንሳት ነገን ለማወቅ ትላንትን ማለፍ እንደሚያስፈልግ ጭምር  አብራራተዋል ፡፡

ድርቅን በተመለከተ በኢትዮጵያ ከ100 ዓመታት በፊት ድርቅ በየ10ዓመቱ ይጠበቅ እንደነበር  ከዚያም በየ7ዓመቱ  ብሎም በየ3 ዓመቱ ዝቅ ብሎ መምጣት መጀመሩን እና ከዚያም በየ አመቱ በኮሪደሩ መኖሩን እና ይህ ደግሞ  የፖለቲካ ችግር ሳይሆን የተፈጥሮ እንደ ተፈጥሮ አየር ጸባይ መታየት እንዳለበት አንስተው ድርቅን እንደ ፖለቲካ መሳርያ ባንጠቀምበት መልካም ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በድርቅ ምክንያት ተርቦ ምንም ሰው እንዳልሞተ እና በዘንድሮ በታሪካችን ለመጀመርያ ጊዜ 3ሚሊየን ሔክታር መሬት መታረሱን፤መንግስት ዛሬም እንደ ትላቱ ፕሮጀክቶችን አጥፎ ይሰራል እንጂ ህዝቡ ሲራብ ዝም እንደማይል አብራርተዋል ፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራትን ለመጠገን የተሄደበትን መንገድ በተመለተ

የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ስብራት ረዘም ላለ ጊዜ የቆየ ነው፡፡ እንደ ብዙ ስብራቶች የወረስነው ነው ግን የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራት ብቻ ቢሆን ምን አልባት በሪፎርሙ በሄድንበት መንገድ ውጤት ይመጣ ነበር፣ ነገር ግን ወዲያው ኮቪድ መጣ፣ ጦርነቶች ተበራከቱ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተስፋፋ፣ዓለም ላይ በሙሉ አዳዲስ ስብራቶች እየተወለዱ ሄዱ ብለዋል፡፡

በእኛ ሁኔታ አለም ላይ ካለው ክራይስስ በተጨማሪ፣የውስጥ ችግራችን በሰፈር እና በቡድን የምናደርጋቸው ግጭቶች፣ እንዲሁም የውጭ ጫናዎች በነዚህ ድምር ስራዎች የማክሮ ኢኮኖሚውን ስብራቶቻችንን በምናስበው ፍጥነት መጠገን አልቻልነም ብለዋል፡፡

የፊዚካል ፖሊሲ አቅጣጫዎቻችን እና  ስራዎቻችን አሁን ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥሉት መንግስታት ጭምር ፋይዳ ሊያመጡ የሚችሉ አንኳር አንኳር ስብራቶች ተጠግነዋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

1ኛው አንኳር ስብራት በፊዚካል ፖሊሲ ለማረቅ የተሞከረ መሆኑን፤ በሰብሲድ እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ላይ በዕዳ መልክ ይከማች የነበረው ሀብት ሲስተማቲካሊ በሪፎርም መልክ ለመቀነስ  የተሄደበት መንገድ ከፍተኛ እመርታ አሳይቷ ብለዋል::

Similar Posts