


“የመገናኛ ብዙኃን የተረጂነት አስተሳሰብን በመለወጥ ዜጎች ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ተረጂነት ሃገራዊ ክብርንም የሚነካ መሆኑን በማስረዳትና ግንዛቤ በመፍጠር በኩል ከፍተኛ ኃላፊነት ተጥሎባችኋል፡፡”
ሰላማዊት ካሳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ ላይ ለሁለት ቀናት የተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳሉት የሰብአዊ ድጋፍ ጠባቂነት አመለካከትን መየቀር የመገናኛ ብዙኃንና የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ኃላፊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም፣ሐብት ያላት ሃገር ናት ያሉት ሰላማዊት ካሳ…

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ምክንያት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም ብለዋል።
ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ በመግለጫቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ተከታዩቹ ይገኙበታል። ማሻሻያው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ የሁለተኛው መካከለኛ ዘመን መርሃ ግብር ምሰሶ የሆኑ አራቱን መሰረታዊ ጉዳዮች ማለትም፦ 1) በሀገሪቱ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታን መፍጠር 2) የንግድ ስራዎችን የሚያሳልጡ የሚያቃልሉና ውጤታማነትን የሚያሻሽሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢን ማሻሻል 3) የዘርፎቹች ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን የማሳደግ እና የመንግስት የማስፈጸም አቅምን…