ሚዲያዎች የአካባቢ ጥበቃ ስራ የሁሉም ዜጎች የእለት ከእለት ልምምድ የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት ቀጣይነት ያላቸው እና ለውጥ የሚያመጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ይዘቶችን መስራት ይጠበቃል።
አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የኢፌዲሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በጋራ በመተባበር የሁለተኛው ዙር የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን መሰረታዊ አላማና ግቦችን፤ እንዲሁም በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ለሚዲያ ባለሙያዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል። አካባቢን ለመጠበቅ እና ጽዱ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚዲያ ባለሞያዎች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ከፍተኛ ሀላፊነት ያለባቸው መሆኑን ገልፀው…