የኮሙኒኬሽን ተቋማት በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የተናበበና የተቀናጀ የመረጃ ተደራሽነትን ይበልጥ ማጠናከር እንዳለባቸው ተገለፀ
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የተናበበና የተቀናጀ መረጃ ከተቋማት ጋር የመለዋወጥ ዐቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ መሻሻል እያመጣ እና ውጤት እየተመዘገበ መሆኑንና ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ አስታውቀዋል። የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የፌዴራል እና የተጠሪ ተቋማት የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የጋራ መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።…