የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት አካሒዷል
በመድረኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል ምላሸና ማብራሪያ የሰጡባቸው ጉዳዮች በአጭሩ እንደሚከተለው ተዘጋጀተዋል፡፡ ከለውጡ በኋላ የተደረገውን የሰላም ጥሪ ለሁሉም የፖለቲካ ታርቲዎች ምንም አይነት ልዩነት ሳይኖር በተመሳሳይ መልኩ መደረጉን አንስተው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም በዲሞክራሲ እና በድርድር፤ በኃሳብ በመትጋት እንጂ በአፈ ሙዝ (በጠመንጃ) ስልጣ እንደማይያዝ በማብራራት፡፡ በአማራ ክልል በተደረገ ህዝባዊ…
