የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር

ከኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ የተላለፈ መልዕክት

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታዩ ፈታኝ ሁኔታዎችን ወደ ዕድል በመቀየር፣ የታላቅነት ጉዞዋን እያረጋገጠች ትገኛለች፡፡ መንግሥት ተግባራዊ እያደረገ ያለው ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ የሪፎርም ሥራዎች የሀገራችንን ስብራት እየጠገኑ ዜጎች በሀገራቸው መጻኢ ዕድል ላይ ስፋ እንዲሰነቁ ያስቻለ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ ያደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚስተዋሉኮኖሚያዊ ጫናዎችን ተቋቁመን ብልጽግናችንን እንድናረጋግጥ የሚያስችለንን መሠረት ጥሏል፡፡ በዲፕሎማሲው ረገድም፣ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅና በቀናዊ ትስስር ላይ የተመሰረተ የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እያጠናከርን እንገኛለን፡፡

ዓለም ዛሬ በዲጂታል አብዮት እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታጀበ ፈጣን የሚዲያና ኮኒኬሽን ለውጥ ላይ ትገኛለች። ይህ የቴክኖሎጂ እድገት መረጃን በፍጥነት ለማድረስ ዕድል የፈጠረ ቢሆንም፣ የሀሰተኛ መረጃዎች (Disinformation) ሥርጭት ግን ለሀገራት ደህንነት ትልቅ ስጋት ሆኗል፡፡ በመሆኑም የመንግሥት ኒኬሽን አገልግሎት ተቋማዊ አቅሙን በማዘመን፣ ዘመናዊ የዲጂታል ሚዲያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እና መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የማደራጀትና የመተንተን አቅሙን በማሳደግ በኩል ሰፊ ሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ግባችን መንግሥት እና ሕዝብ በመረጃ እንዲጣመሩና እንዲተሳሰሩ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ተወዳዳሪና ተዓማኒ የሚዲያና ኮኒኬሽን ሥርዓትን በመገንባት የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገጽታ ለዓለም ማስተዋወቅ ነው፡፡

የኢትዮጵያዊነት ጽኑ መሠረት የሆነው አንድነታችን ለገጠሙን ተግዳሮቶች ሁሉ ዋነኛው መፍትሔ ነው፡፡ ተቋማችን ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትንና ወቅታዊ መረጃን መርሁ በማድረግ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን መተማመን ለማጠናከር በትጋት እየሰራ ነው፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የኢትዮጵያን ትክክለኛ ምስልና እዉነታዎችን በተሟላ መረጃ አጀንዳ በመቅረጽ፣ በማረጋገጥ ዲሞክራሲያዊ ባህልን በመገንባት ሀገራዊ የልማት ግቦችን ከዳር የማድረስ ሀላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ 

ይህን ሃላፊነት ለመወጣት ስትራቴጂካዊ አመራር፣ ፈጠራ እና ፍጥነት ይጠይቃል፡፡ ሕዝባችንም ከሀሰተኛ መረጃዎችና ከከፋፋይ አጀንዳዎች ራሱን በመጠበቅ፣ በሀገረ መንግስት እና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታዎች

ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚዲያ ግንኙነት ክትትልና መረጃ ማደራጃ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

ክቡር አቶ ከበደ ደሲሳ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት እና ተቋማት ማስተባበርያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ