የሰንደቅ አለማ ልዕልና የሚገለጠው ሰንደቅ አለማውን በሰቀልንበት የከፍታ ማማ ነው ።
ሠንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ የአንድ አገር ዜጎች አገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜትን የሚገልፁበት፤ ታሪካዊ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚንፀባረቁበት የአገራዊ አንድነትና ህብረት አርማ ነው።
በአገራችን ኢትዮጵያ ለአስራ ስምንተኛ /18ኛ/ ጊዜ “ሰንደቅ ዓለማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የክፍታ ዘመን ብስራት ለብሔራዊ አንድነታችን ፣ለሉዐላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ !” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም በደማቅ ስነ ስርዓት አክብሯል፡፡
በክብረ በዓሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ክብርት እናትአለም መለሰ ባስተላለፉት መልዕክት የዘንድሮ የሰንደቅ ዓለማ በዓል ለየት የሚያደርገው የመቻላችን ማሳያ የሆኑትን ትልልቅ ፕሮጀክቶች በፈጸምንበት ማግሥት የምናከብረው በዓል መሆኑ ነው ያሉ ሲሆን በተለይ ዳግማዊ ዐደዋ የሆነው የህዳሴው ግድብ ፣የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ፕሮጀክት እና ሌሎች በዜጎች ህይወት መሻሻል ላይ ተጽዕኖአቸው የጎላ ሚጋ ፕሮጀክቶችችን መመረቃቸው በዓሉን ልዩ ያደረገዋል በለዋል ።
የእነዚህ ፕሮጀክቶች መመረቅ ለዘመናት የተበተቡንን የኋላ ቀርነት ገመድ የበጣጠሱ ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ ሁላችንም በተሰማራበት መስክ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ለማስቀጠል በሀገራዊ ፍቅር ስሜት፣ አባቶቻችን ባስረከቡበን ሰንደቅዓላማ ስር በአንድነት ጠንክረን መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል ።
በመጨረሻም ሰንደቅ አላማችን የአትዮጵያ ህዝቦች እኩልነት፣ አንድነት፣ ማንነትና ሕብረ-ብሄራዊነት መገለጫ እንዲሁም የሉዓላዊነታችን መሰረት መሆኑን የጠቀሱት የአገልግሎቱ ሚኒሰትር ታሪክ ሠርተው ሰንደቅ አላማችንን ላስረከቡ አባቶቻችን ምስጋና አቅርበዋል።
የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
18ተኛው የሰንደቅዓላማ ቀን በፓናል ውይይትና በተለያዩ መርሀግብሮች አክብሯል ።


