ባለፉት 100 ቀናት የዉጭ ቱሪስት ፍሰት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል- የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)
ባለፉት 100 ቀናት ዉስጥ የዉጭ ቱርዝም ፍሰት ከዕቅድ ከተያዘዉ በላይ በመጨመር በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዉስጥ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
በዚህም በ100 ቀናት ብቻ 376ሺህ 615 የዉጭ ቱርስቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል ብለዋል፡፡ ይህም በዕቅድ ከተያዘዉ 150% ማሳካት የተቻለ ሲሆን፣ ከአምና በተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡
በተለይም ባለፉት ሶስት ወራት ዉስጥ 29 የአለም አቀፍ ሆነቶች በአዲስ አበባ የተካሄዱ በመሆኑ የቱርዝም ዘርፉን በማነቃቃት ረገድ ስኬታማ ስራዎች መሰራታቸዉን ዶ/ር ፍጹም አብራርተዋል፡፡
በአዲስ አበባ በተካሄዱ የዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶች ላይ የተለያዩ የዓለም ሀገራት መሪዎች፣ የቢዝነስ ተቋማት አመራሮች፣ ተመራማሪዎችና ሌሎች አካላት መሳተፋቸዉን አስታዉሰዋል፡
በተካሄዱ የዓለም አቀፍ ሁኔቶች በተለይ ኢትዮጵያን ከማስተዋወቅ በሻገር እንደ ሀገር አቅማችንን ያሳየንበትና በርካታ የዉጭ ቱርስቶችን ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ ማስተናገድ መቻላችን ትልቅ ስኬት ነዉ ብለዋል፡፡



