የኢትዮጵያን አቅም ላኪው ያውቀዋል ተላላኪው ግን ይጓጓል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያን አቅም ላኪው ያውቀዋል ተላላኪው ግን ይጓጓል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያን ዕድገት የማይፈልጉ ሀገራት በጦርነት ሊያሸንፉን እንደማይችሉ ያውቁታል። ነገር ግን የኢትዮጵያን አቅም ላኪው ቢያውቀውም ተላላኪው ግን ይጓጓል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ኢትዮጵያ ደካማ ሆና እንድትኖር ኢትዮጵያ በሁለት እግሯ መቆም እንዳትችል የሚሹና የሚሰሩ ሀገራት ባሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምን ለይተው ማወቅ ካልቻሉ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ እና ለጠላት ፍላጎትና ጥያቄዎች ተላልፈው ከተሰጡ የተሟላ ሰላም ማምጣት ይቸግራል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ስለ ፀጥታ ጉዳይ ምላሽ ሲሰጡ ኢትዮጵያ ለመገንጠልም ለመጠቅለልም አትመችም። ነገር ግን ፍላጎታቸውን ለማሳካት ቀላል መንገድ የሚመስላቸው ከጠላት ጋር ማበር ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
ከታሪክ መማር ቢቻል ኖሮ በድፍን አፍሪካ የመሳሪያ አፈሙዝ ይዘው፣ መንግስታትን ተቃርነው ተዋግተው አሸንፈው ላሸነፉት ሀገር ልማትና ዴሞክራሲ ያመጣ አንድ ሀገር የለም፣ ታጥቆ ይመጣል ታጥቆ ይመለሳል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመሳሪያ የሚመጡ ሰዎች ከመሳሪያ ያለፈ ነገር ማሰብ እንደማይችሉና ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ብቻ እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
እኛ እንደ መንግስት እንደ መፍትሔ የምንወስደው ችግር አለብኝ የሚል የትኛውም ኃይል ጋር መወያየትን ነው ለዚህም ሸኔ ጋር እና ከትግራይ ጋር ደረጉትን ውይይት እና ወደ ሰላም የመጡትን ማየት እንደሚቻል ጨምረው ገልጸዋል፡፡


