ረቡዕ መስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ብሔራዊ የአትዮጵያ ዘመን መለወጫ ቀን

መስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ – ያ ሆዴ በዓል
በደቡብ ክፍሎች ውስጥ ለአንድ ወር በድምቀት የሚከበር የዘመን መለወጫ በዓል
ነው፡፡
መስከረም 5/6 ቀን 2017 ዓ.ም መውሊድ በዓል
ነቢዩ መሓመድ የተወለዱበት ቀን እስበልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ
የሚከበር በዓል ነው፡፡
ዓርብ መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ማሽቃሮ ባሮ በዓል
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የዘመን መለወጫ በዓል ነው፡፡
መስከረም 13/14 ቀን 2017 ዓ.ም ሸዋል ኢድ በሐረር
ቱሪዝም ሚኒስቴር
መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም ሄቦ በዓል
የሄቦ በዓል በየም ብሔረሰብ የሚከበር ድንቅ ባህላዊ እሴት ነው፡፡
መስከረም ከ14-20 ቀናት 2017 ዓ.ም ጊፋታ በዓል
በወላይታ ሕዝብ ዘንድ ከአሮጌው ወደ ዐዲሱ ዓመት የመሸጋገሪያ በዓል ጊፋታ ይባላል፡፡
መስከረም 15 ቀን ጋሮዎሬ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዘመን መለወጫ በዓል
መስከረም 16 እና 17 ቀን 2017 ዓ.ም ደመራ እና መስቀል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በድምቀት
ይከበራል፡፡ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ በዓል ነው፡፡
መስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም ዮ መስቀላ
የጎፋ ሕዝብ በታላቅ ድምቀት የሚያከብረው የዘመን መለወጫና የመስቀል በዓል ነው፡፡
መስከረም 17 ቀን የዓለም የቱሪዝም ቀን
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የዓለም ቱሪዝም ቀን በኢትዮጵያም
በልዩ ኹኔታ በየዓመቱ ይከበራል፡፡
ዓርብ መስከረም 17/17ዓ.ም ጎፋ ገዜ በዓል
የጎፋ ዞን ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ነዉ
ዓርብ መስከረም 17/17 ዓ.ም አይዳ ዮኦ ማስቃላ
የአይዳ ሕዝብ ዘመን መለወጫ ተብሎ ይከበራል።
መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም የግሸን ደብረ ከርቤ ንግሥ በዓል
በደቡብ ወሎ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች
ዘንድ የሚከበር ዓመታዊ የንግሥት በዓል ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቈጠሩ የሀገር ውስጥና
የውጭ ሀገር ምዕመናንና ጎብኝዎች ይደሙበታል፡፡
መስከረም 25 እና 26 2017 ዓ.ም እሬቻ በዓል
የኦሮሞ ሕዝብ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት ሆራ ፊንፊኔና ሆራ አርሰዲ ለይ የሚደረግ
በዓል ነው፡፡ አዲስ አበባ አስተዳደር፤ ኦሮሚያ ክልል፤ ቱሪዝም ሚኒስቴር ከሕዝብ ጋር
በዓሉን ያከብሩታል፡፡ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ በዓልም ነው፡፡
ማክሰኞ መስከረም 28/17 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ስደተኛ አዕዋፋት ቀን
ቱሪዝም ሚኒስቴር

Similar Posts