“ኢትዮጵያ ታሪኳን በራሷ ልጆች እየጻፈች መሆኑን የ100 ቀናት ሪፖርት ማሳያ ነዉ” ወ/ሮ እናትአለም መለሰ

የዓለም መሪዎች በ100 ቀናት የሰሩት ስራዎች ላይ ዜናዎች እንደሚወጣ ያነሱት የመንግሥት ኮሙኒኬሺን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትአለም መለስ በአፍሪካ ግን ይህ አሰራር ያልተለመደ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የአፍሪካ መሪዎች አያልሙም ካለሙም አይተገብሩም የሚል ትቺት እንዳለም ግልፀዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ በኢትዮጵያ በ100 ቀናት ዉስጥ የሚነገር ታሪክ ነጥሎ ያየ፤ ሃሳቡን መሬት የሚያወርድ፤ አካሄዱን ደግሞ በትክክል ከህዝብ ተጠቃሚነት ጋር ማቆራኘት የሚችል አመራር በማየት በመቻሉ ኢትዮጵያ ታሪኳን እየጻፈች መሆኑን ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡

በዚህም ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እና በዚህ እንዲኮሩ የሚያደርግ ታሪክ በራሷ ልጆች እየተጻፈ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ እናትአለም፤ ዜጎች ራሳቸዉንና ታሪካቸዉን ከመቀየር አልፈዉ ለገበያ የሚቀርብ ምርት በማምረት በየቀኑ ተደማሪ የኢኮኖሚ ታሪክ እየተፃፈ መሆኑን ከ100 ቀናት ሪፖርት መረዳታቸዉን ገልፀዋል፡፡

የፋብሪካዎች ምርት መጨመርም እስከ ዛሬ ከእጃችን ሲያመልጥ የነበረዉን መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር ለዉጥን መጨበጥ መቻሉን አንስተዋል፡፡ ይህ ስኬት ትርጉም ያለዉ፤ ለትዉልድ የሚነገር፤ የሚጻፍ ታሪክ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ከሁሉ በላይ ግን ኢትዮጵያ በራሷ አቅም፤ በገነባችው የኢኮኖሚ ተቋማት ገንዘብ የምትሰራ ሀገር መሆኗን ገልፀዋል፡፡ በዚህም ዜጎች የሀገርን ሃብት ያለምንም ልዩነት ተበድረዉ መስራት የሚችሉበት እድል መፈጠሩንም አንስተዋል፡፡

Similar Posts