ኢትዮጵያ የብዝሃ ኢኮኖሚ ፖሊሲን በመከተሏ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች ተመዝግቧል _ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዎች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሳባ ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በኢኮኖሚው ዘርፍ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ኢትዮጵያ የብዝሃ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመከተሏ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከዚህ ቀደም ግብርና መር የነበረው፣ አሁን ግብርናን ጨምሮ በማኑፋክቸሪንግ ፣በማዕድን፣ በቱሪዝም ፣በእንዱስትሪ እና በተክኖሎጂ ዘርፎች በሚደጋገፉ መልክ ተሰረተው ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገቡን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጿል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ ለሕዝብ ተወካዎች ምክር ቤት በሰጡት ምላሽ እና ማብራርያ፣ መንግሥት ሀገሪቱ በሁሉም መስክ ስር-ነቀል ዉጤት እንዲያመጡ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህም በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣መዕድንና፣ቱርዝም እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ተጨባጭ ዉጤቶችን ማስመዘገብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ሲኬቱም በመንግስት እና በህዝብ በተቀናጀ ርብርብ መሳካት ተችለዋል ብለዋል፡፡
የብዝሃ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ሪፎርም በተግባር የተረጋገጠ ሲሆን የሪፎርሙ ዋና ዋና አላለማዎች፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማዛባት ማድረቅ ፣የንግድ እና እንቨስትምንት ከባቢን ማሻሻል፣የዘርፎችን ምረታማነትና ተወዳደሪነት አቅማቸውን ማሳደግ፣ የማስፈጻም አቀቅማችን ማሻሻልና ማሰደግ፣ዘላቂ የፈይናንስ ስርዓት ማሻሻል ናቸው ሲሉ ገልጾዋል፡፡
በዚህ ዓመት ብቻ ግብርና 7 ነጥብ 3 ፐርሰንት እድገት አሳይቶዋል፤ ይህም 2.3 የGDP አስተዋጽኦ አለው፤ ሩዝ 33 ሚሊየን ኩንታል፣ ስንዴ በመዝራት እና ከፍተኛ ድርሻ ያለው ምርጥ ዘር በመጠቀም ከ280 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ተጠቅሰዋል። ቡና 11.5 ሚሊየን ኩንታል ተመርተዋል። አጠቃላይ ከግብርና የተገኙ ዉጤቶች ከፍተኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል ፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራርያ ፣ እንዱስትሪ በ13 ፐርሰንት አድጎዋል ይህም ከሀገራችን እድገት GDP ዉስጥ 3.4 ፐርሰንት ድርሻ እንዳለው ጠቅላይ ሚንስተሩ ገልጸዋል።
የማዕድን ዘርፍ ደግሞ የነበረው የGDP እድገት ከ0.1 ወደ 1ፐርሰንት አድጎዋል፡፡
የኑሮ ዉድነት ለመሻሻል መንግስት 440 ቢልየን ብር ድጎማ አድርጎዋል፡፡ በዚህም 11.7 የኑሩ ዉድነት በመቀነስ ከሪፎርሙ ዘመን ጀምሮ ትንሹ የዋጋ ንረት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ይህም ዉጤት የተገኘ በተሰራው ሪፎርም እና ሁሉን አቀፍ ስራዎች በመሰራታቸው ሲሆን፣ በሴፍትኔት፣ በማዳበርያ፣ በነዳጅ እና ደምወዝ ለይ ድጎማ ማድረግ እና በግብርና ሰፊ ስራ በመሰራቱ ትስስር በመፍጠር ቀጥታ በማቅረብ፣ የእሁድ ገበያ በማቋቋም ነዉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማብራርያቸውን ሰተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሪፎርም እኛም ሌሎችም አጋሮቻችንም ከሚጠብቁ በላይ ስኬታማ መሆኑን እና ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት ባለሁለት አሃዝ እድገት ታስመዘግባለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚንስተሩ አበራርተዋል፡፡

