ክብርት እናትዓለም መለሰ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቀባበል ተደረገላቸው፡፡
መስከረም 09 ቀን 2018 ዓ.ም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር በመኾን የተሾሙት ክብርት እናትዓለም መለሰ ዛሬ በአገልግሎቱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ከአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋርም ትውውቅ አድርገዋል፡፡
*************


