የኢትዮጵያ ዕድገት ለመላው አፍሪካ ምሳሌ ተደርጎ የሚወሰድ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ዕድገት ለመላው አፍሪካ ምሳሌ ተደርጎ የሚወሰድ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ዕድገት ለመላው አፍሪካ ምሳሌ ተደርጎ የሚወሰድ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ገለፁ፡፡
የኢትዮጵያ የአሁን ዕድገት ጥሩ አፍንጫ ያለው ሰው ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀስ በሽታ ያውቀዋል፣ ጥሩ ዐይን ያለውም ሰው በማየት የኢትዮጵያን ዕድገት ይገነዘባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እኛ እንደሚታወቀው ሳሎን ማሳመርና ጓሮ ማቆሸሽ ቋሚ ልምምዳችን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በበሬ እያረሰ የከረመ ህዝብ ትራክተር ሲመጣ የሚተወው ልምምድ እንዳለ ግልጽ እንደሆነና የሚቀየሩ ባህሎች ሲኖሩ ሰው ከልማዱ ጋር ለመፋታት እንደሚቸገር ነገር ግን ኮሪደር ልማት ከፍተኛ የፈጠራ አቅምን እያመጣ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ በአዲስ አበባ ከ1000 በላይ ስታዲየሞችን የተገነቡ ሲሆን ወጣቶችን እንዲሁም ጎልማሶችን ከተለያዩ የሱስ ቦታዎች በመታደግ ወደ ካስ ሜዳና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲገቡ በር ከፍቷል፡፡

