“የኮይሻ ፕሮጀክት እንደ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ብቻ ሳይሆን የቱሪዝም መስህብ የሚሆኑ ስራዎች አሉት” ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህ
የኮይሻ ፕሮጀክት ከኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት ባሻገር የቱሪዝም መስህብ የሚሆኑ ገፅታዎች እንዳሉት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘የሚኒስትሮች ምክር ቤት ምልከታ በኮይሻ’ በሚል በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መንግስት በለውጡ የታደገው ሌላው ፕሮጀክት የኮይሻን ፕሮጀክት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የዱር እንስሳት መገኛ የሆነው እና አረንጓዴ የለበሰውን የጨበራ ጩርጩራ ለምለም ምድር ቱሪስቶች ሲጎበኙት ማየታቸውን ገልጸው፤ ወደፊትም በበለጠ መልኩ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን ከኮይሻና ከሌሎች መስህቦች ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባም አሳስበዋል።

