የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት!!
በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረግነው ጥልቅ ውይይት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመሰግናለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነታችን እያደገ ቀጥሏል። ከዚህ በተጨማሪ የጋራችን የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል።

በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረግነው ጥልቅ ውይይት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመሰግናለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነታችን እያደገ ቀጥሏል። ከዚህ በተጨማሪ የጋራችን የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል።
ዓለም በአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት ተጠቃሚነታችንን ለማረጋገጥ እና ወጣቱ በአዲሱ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ስኬታማ እንዲሆን በንቃት መሥራት ይጠበቅብናል። በአሁኑ ወቅት እንደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence)፣ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ፣ ናኖ ቴክኖሎጂ እና ቢግ ዳታ ባሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የሚደገፉ የማምረት፣ የመገናኛ እና የአኗኗር ዘዬ ሽግግርን እየተመለከትን ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ዲጂታል ከባቢ እና ቴክኖሎጂን…
በቅርቡ የአለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት USAID ለኢትዮጵያ የሚያቀርቡትን ሰብአዊ ድጋፍ ለጊዜው መግታታቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ መንግስት ከአጋር አካላቱ ጋር በጋራ በመሆን የአሰራር ክፍተት አለባቸው የተባሉትን ለመፈተሽ፤ ማሻሻያ ለማድረግና ህገወጥ ተግባራትም ተፈፅመው ከተገኙ አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል። ይህንንም ተከትሎ በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መሪነት ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት…
**************************** የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሀገራዊ የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡ በበይነ መረብ በተካሄደዉ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የክልል እና ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ተቋማት እና የፌዴራል ተቋማት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ የአገልግሎቱ፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ተቋማት እና የፌዴራል ተቋማት የሕዝብ ግንኙነት የሥራ ክፍሎች የሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሞች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡…
ፕሬዚዳንቱ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክርቤቶች 4ኛ የሥራ ዘመን የጋራ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር ላይ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ በኢኮኖሚ ዘርፍ ከሚደረጉት ጥረቶች በታክስ መረቡ ያልገቡትን ወደታክስ መረቡ በማስገባትና አዳዲስ የታክስ ምንጮችን በማካተት አጠቃላይ የመንግስትን ገቢ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ለማድረስ ይሰራል ብለዋል፡፡ ከታክስ የሚሰበሰበው ገቢ አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ገቢ የሚኖረው ድርሻ 8 ነጥብ 3 በመቶ…
5 Million Coders መመዝገቢያ ሊንክ http://www.ethiocoders.et/ የ5000000 የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሽዬቲቭ የኢትዮጵያ ወጣቶች ተገቢውን የሆነ በአለምአቀፍ ደረጃ ተፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጂ እንደዚሁም የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ የተቀረጹ ፕሮግራሞች ናቸው ይሄ ስልጠና ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 3 ወራት ውስጥ ከ242 ሺህ በላይ አሰልጣኞች ተመዝግበው ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛል በአጠቃላይ ከተመዘገቡት ውስጥ ከ81 ሺህ በላይ የሚሆኑት በመሰረታዊ ፕሮግራሚንግ ስልጠና…