መንግሥት የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ዛሬም እንደ ትናንቱ በትጋት ይሠራል፡፡
የአማራ ክልል ሕዝብ ባለፉት ጥቂት ዓመታት መክፈል የማይገባዉን ውድ ዋጋ በጥቂት ጥቅመኞች ምክንያት እየከፈለ ይገኛል፡፡ የፋኖን ታሪካዊ አነሣሥ እና ዓላማ ባልተከተለ አግባብ ራሳቸዉን በፋኖ ስም የሚጠሩ ፅንፈኛ ኃይሎች በቀሰቀሱት ግጭት የአማራ ክልል ሰላም እና ልማት ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ ፋኖ ሀገር በባዕድ ወራሪ እጅ በወደቀችበት እና ማእከላዊ መንግሥት በግዞት በቆየበት ወቅት ሀገርን ለማዳን የተደረገ ተጋድሎ የተመራበት ድንቅ…
