አረንጓዴ አሻራ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ነዉ _ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
(ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም) አረንጓዴ አሻራ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና አጠቃላይ ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር ዘነበወርቅ የሚገኘዉ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጧል፡፡ በኢቢሲ ግቢ በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በርካታ የቡና ችግኞች ተተክለዋል፡፡…
