የአፍሪካ-ጣሊያን ጉባኤ በአፍሪካ አፈር ሲካሄድ የመጀመሪያ መዳረሻውን ኢትዮጵያ አድርጓል
የአፍሪካ-ጣሊያን ጉባኤ በኢትዮጵያ መካሄዱ የአፍሪካ-ጣሊያን ግንኙነት በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የትብብር ማዕቀፎች ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያደርግ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የአፍሪካ-ጣሊያን ፎረም መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከሮም ውጭ ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያው ነው ያሉት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ በአፍሪካ አፈር ሲካሄድ የመጀመሪያዋ መዳረሻ ኢትዮጵያ መሆኗ ሀገራችን አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ከማስተሳሰር አንጻር ያላትን…

