የኢትዮጵያ መንግስት ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጣው ሪፖርት ተቀባይነት እንደሌለው አስታወቀ፡፡
መንግስት ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ምላሹም እንደሚከተለው ይቀርባል፡- ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ድርጅት እ.ኤ.አ. ጁን 1 ቀን 2023 (ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም) በሀገራችን በአንዳንድ አካባቢዎች ጉልህ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚገልጽ መሰረተ ቢስ ሪፖርት አውጥቷል ብሏል። በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ግጭት በርካታ አካባቢዎችን ለጉዳት ያጋለጠ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የተወሰነ…
