ኢትዮጵያ በ2015 ዓ.ም ከውስጥና ከውጪ በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሟትም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቧን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በአዳማ የፌዴራል እና የክልል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዓመታዊ የጋራ መድረክን ሲከፍቱ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአሁኑ ወቅት ከአፍሪካ 5ኛ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ደረጃ ላይ መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡ በሃገሪቱ የተመዘገቡት ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ሁሉም ጠንካራ የሚዲያና እና የኮሙኒኬሽን ተግባቦት ሥራ ድጋፍ እንደነበራቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ ስኬቶቹ ግን በርካታ ፈተናዎችም እንደነበሩባቸው ጠቁመዋል፡፡ በተለይም ጽንፈኝነትና አክራሪነት እንደ…
