ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ እና ዐቅም ነው! ********************************
ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ ብዝኃ ማንነት ደምቃ፣ ፀንታና ታፍራ የኖረች፣ ብዝኃ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት የሆነች ድንቅ ሀገር ናት፡፡ ብዝኃነታችን የጥንካሬያችን፣ የሥልጣኔያችን፣ የአይበገሬነታችን፣ የክብራችን፣ የነፃነታችን እና የአልሸነፍ ባይነታችን ምሥጢር ነው፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቦታዎች እና የኪነ ሕንጻ ሀብቶቻችን የብዝኃነታችን ውጤቶች ናቸው፡፡ የአክሱም ሐውልቶች፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የለጋ ኦዳ ዋሻ…
