ዛሬ ቀኑ ሃምሌ 10 ነው!

|

ኢትዮጵያውያን ዳግም ለትውልድ የሚሻገር ታሪክ ለምንሰራበት ቀን እንኳን አደረሰን!

#GreenLegacy🇪🇹

ኢትዮጵያዊያን ማቀድ፤ መተግበርና፤ በትጋት ሰርቶ መፈፀም ብቻ ሳይሆን የጀመርነውን ማስቀጠል እንደምንችል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተግባር አሳይተናል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ገለፁ፡፡

ሚኒስተር ዴኤታዋ ዛሬ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃግብር መጀመርን አስመልክቶ አዲስ አበባ ከሚገኘው የሁኔታ መከታተያ ማዕከል መግለጫ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም የራሳቸውን ክብረወሰን የሚያሻሽሉበት ታሪካዊ ቀን ነው ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በትላንትናው እለት የራሳችንን ሪከርድ እንስበር በማለት ያሰተላላፉት ጥሪ ዛሬ ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ በመላው ሃሪቱ መተግበር ጀምሯል ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታዋ።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለዛሬው እለት በልዩ ሁኔታ በመላ ሃሪቱ ወደተዘጋጁት ከ9 ሺህ በላይ የችግኝ መትከያ ጣቢያዎች በመሄድና ችግኞችን በመትከል ለትውልድ የሚሻገር ታሪክ እንዲሰራ ሚኒስትር ዲኤታዋ ጥሪ አቅርበዋል

Similar Posts