የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት!!
በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረግነው ጥልቅ ውይይት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመሰግናለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነታችን እያደገ ቀጥሏል። ከዚህ በተጨማሪ የጋራችን የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል።

በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረግነው ጥልቅ ውይይት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመሰግናለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነታችን እያደገ ቀጥሏል። ከዚህ በተጨማሪ የጋራችን የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል።

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጥቅምት 22/2018 መንግሥት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማን ለመገንባት የኮሪደር ልማቱን ከአዲስ አበባ በመጀመር በሁሉም ክልሎች እንዲስፋፉ የሚያደረጉ ከተማን የማልማት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ የኮሪደር ልማት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ከማረጋገጥ አኳያ የጎላ ሚና አበርክቷል ፡፡ በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ቀስበቀስ የሁሉም ከተሞች ልምድና ባህል ወደ መሆን ተሸጋግሯል ። የአዲስ አበባ ከተማ ከኮሪደር ልማቱ በፊት…
መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለጳጉሜ 5 የነገ ቀን እና ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሠላም አደረሳችሁ! ነገ የጊዜ መቍጠሪያ ብቻ አይደለም፤ ነገ ተስፋ፣ ምኞት፣ ስንቅ፣ ለዛሬ መነሣሣትና ትጋት ምክንያት ጭምር ነው፡፡ ነገ ሁላችንም ለማየት የምንጓጓለት፣ የተሻለ ሕይወትና ስኬት እንዲኖረን የምንመኘዉ መሻታችን ነው፡፡ እንደግለሰብ የተሻለ ነገን እንመኛለን፤ እንደቤተሰብ የተሻለና የጋራ ደስታና ተድላ ያለው ነገን እናልማለን፤ እንደሀገር ሰላም፣ ደስታ፣ ብልጽግና…
የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል “ፅዱ ኢትዮጵያ” በሚል መጠሪያ ሁለተኛዉ ሀገራዊ ንቅናቄ ዛሬ ተጀምሯል። ንቅናቄዉ በአካባቢ ጥበቃ ጽዱና አረንጓዴ ኢትዮጵያን በመፍጠር ለመጪው ትውልድ ኹለንተናዊ ምቹ ሀገር የማስረከቡ ጥረት አካል ነው። ጽዱ እና ምቹ ኢትዮጵያን ለትውልድ የማስረከብ ጉዞዉ የሚሳካው በየደረጃው ያሉ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን አካላት ጉዳዩን በጥልቀት ተገንዝበዉ ለማኅበረሰብ በማስረዳት እና ሥራዎችን በባለቤትነት ሲመሩ መኾኑ ተገልጿል። የንቅናቄው ማስጀመሪያ አካል…
ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት በፊት የተጀመረዉን የዲጂታል ማንነት ሥርዓት የመገንባት ጉዞን እዉን በማድረግ ላይ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመድ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተጀመረዉን የአይዲ ፎር አፍሪካ 2025 ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት “ፋይዳ” መሰረታዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምሶሶ አካል መሆኑን…
ቀን-21-12-2017 የአፍሪካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የኅብረቱ አጀንዳ 2063 እንዲሳካ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ባህል ትስስር መጠናከር ላይ እንዲያተኩር የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር) አሳሰቡ፡፡ 15ኛዉ የምሥራቅ አፍሪካ የኮሙኒኬሽን ማኅበር (East African Communication Association) ኮንፈረንስ አዲስ አበባ ላይ እየተካሄደ ነው፡፡ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር)…