19ኛው የብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በተቋም ደረጃ በድምቀት ተከበረ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017(የኢፌዴሪ መ.ኮ.አ)

“ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት “በሚል መሪ  ቃል  19ኛው የብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በዛሬው ዕለት ተከብሯል ።

በመርሐ ግብሩ  የአገልግሎቱ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ለገሠ ቱሉን ጨምሮ ክቡር ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ እና የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ዝናቡ ቱኑ ተገኝተዋል ።

በዓሉ በተለያዩ ሁነቶች የተከበረ ሲሆን የፓናል ውይይት፤ የጥያቄና መልስ ፕሮግራሞችና የመድረክ ሴሬሞኒዎች የዝግጅቱ ድምቀቶች ነበሩ።

ለፓናል ውይይቱ የተዘጋጀው ሰነድ በአቶ እንዳለው ሙሉዓለም ቀረቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በአገልግሎቱ ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባችዋል ።

መልካቸው ቢቀያየርም ከ1960ዎቹ በኋላ የኢትዮጵያዊያን ጥያቄዎች የመሬት ፥የብሔረሰብ መብት እና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ነበሩ ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ከዴሞክራሲ ጥያቄ በቀር የመሬትና የማንነት ጥያቄዎችን ለመመለስ በጊዜው በነበሩት መንግስታት   በጥቂቱም ቢሆን ሙከራዎች ሲደረጉ ነበሩ ብለዋል ።

ብልጽግና ከተመሠረተ ወዲህ ግን  ያለፉ ዘመናትን ስብራቶችን በመጠገን ለእውነተኛ ፌዴራሊዝም ሥርዓት ግንባታ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሠራ ይገኛል ያሉት  ዶክተር ለገሰ፤ ዛሬ ላይ በሁሉም ክልሎች የሞግዚት አስተዳደር ተወግዶ ብሔር ብሔረሰቦች በዴሞክራሲያዊ መንገድ  ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩት አውድ ተፈጥሯል ብለዋል።

Similar Posts