ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ያላት ብዝኃነት ልዩ ዐቅም የሚፈጥርላት መሆኑ ተገለፀ።

ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥበሚል መሪ መልእክት የኅብር ቀን በመላዉ ኢትዮጵያ እየተከበረ ነው፡፡ ብዝኃነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል፣ ብዝኃነት ለኢትዮጵያ ያበረከተዉን ፋይዳ እና በቀጣይም በላቀ ደረጃ እንዴት መጠቀም እንደሚገባ የሚያስገነዘብ የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ጥንታዊና ገናና ታሪክ ካላቸዉ፣ የበርካታ እና ማራኪ ብዝኃ ሕይወት ባለቤቷ ኢትዮጵያ ብዝኃ ማንነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት ያላቸውና ተፈቃቅደዉ በጋራ ታሪክ እየሠሩ የቀጠሉ ሕዝቦች ሀገር መኾኗን አመላክተዋል፡፡ኢትዮጵያውያንን የሚያስተሳስሩን የጋራ ድሎች እና ታሪኮች አሉን፤ ቀደምቶቻችን በጋራ ጠላትን መክተዉ ነፃ ሀገር አስረክበውናል፡፡ እኛም በጋራ ታላቁ ሕዳሴ ግድብን አሳክተናል፤ በዚህ የወል ድላችን በመስፈንጠር ኢትዮጵያን ወደ ከፍታዋ ማድረስ ይኖርብናልሲሉም አቶ መሐመድ አስገንዝበዋል፡፡

የፓናል ውይይቱን የመሩት የፍትሕ ሚኒስትር ሐና አርዓያሥላሴ ደግሞኢትዮጵያ የብዙ ብዝኃነት ሀገር ነች፤ ከቋንቋ፣ ባህልና ሃይማኖት ባሻገር ለኅብር መሠረት የኾኑ የመልክአ ምድር፣ የአየር ንብረት፣ የታሪክ እና የመሳሰሉት ብዝኃነቶች አሏት፡፡ ይህ ብዝኃነታችን ደግሞ እንደ ዓድዋ እና ኅዳሴ ያሉ የወል ድሎች ያስተሳስሩታልብለዋል፡፡ የፓናል ውይይቱ ብዝኃነትን የበለጠ ጠንካራ መሠረት ለማስያዝና ለማጠናከርና የወል ትርክት በመፍጠር ላይ የጎላ ሚና እንደሚኖረዉ ገልጸዋል፡፡

የጋራ ታሪክ እና ባህል ለብዝኃ ማንነትበሚል ርእስ የፓናል መነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴየጋራ ባህልና ታሪክ መገለጫዎች፣ የጋራ ባህልና ታሪክ ለምን እና እንዴት እየተሸረሸሩ መጡ፣ መልሶ ለመገንባትስ ምን ማድረግ ይኖርብናል?” የሚሉትን ጥያቄዎች የዳሰሰ ገለጻ አቅርበዋል፡፡

ማኅበራዊ ባህላዊ እሴቶቻችን ለአዎንታዊ ሰላማችንና አብሮነታችንበሚል ጭብጥ ላይ ተመሥርተዉ የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡት ደግሞ . ተካልኝ አያሌዉ ናቸው፡፡ በጽሑፋቸዉም በሕዝቦች የረዥም ዘመን መልካም ግንኙነት የተገነባ ማኅበራዊ ሀብት መኖሩንና ማኅበረሰብን አጣመሪ እና አሻጋሪ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡ የጋራ መተማመን የሚፈጥሩ፣ የጋራ ግንዛቤ እና መተማመን የሚፈጥሩ፣ የወል ማንነት የሚገነባበት፣ የጋራ ደንቦች እና እሴቶች የሚፈጠሩበት ማኅበራዊ ሀብት መኖሩንም . ተካልኝ አብራርተዋል፡፡ ማኅበራዊ ሀብቶች ማኅበራዊ ቁርሾዎችን ማከሚያ መድኃኒቶች እንደኾኑም ገልጸዋል፡፡

ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት ግንባታ የሚዲያ ሚናን በተመለከተ ደግሞ . ተስፋዬ በዛብህ የመነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ ኅብረ ብሔራዊ ሚዲያ የተዛባ አመለካከትን የመግራት፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን የማጋለጥ እና እውነታን መሠረት ያደረገ መረጃ የማድረስ ሚናውን ሲወጣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን እንደሚያጠናክር . ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሚዲያ ከመቶ ዓመታት የተሻገረ ታሪክ ቢኖረዉም ዕድገቱ በየሥርዐተ መንግሥቱ በነበሩ ጫናዎች በአግባቡ አለመዳበሩን ያብራሩት . ተስፋዬ ከለውጡ ማግሥት የሚዲያ ነፃነት በከፍተኛ ደረጃ መሻሻሉን ተናግረዋል፡፡

በስደት የነበሩ ሚዲያዎች ወደሀገር መግባታቸዉንና ተዘግተዉ የነበሩ ድረገጾች መለቀቃቸዉን፣ የፀረ ሽብር ዐዋጁ መሻሻሉ እና ሌሎችም ርምጃዎች መወሰዳቸዉ ለሚዲያዉ ብዝኃነት መጠናከር አስተዋጽኦ ማድረጋቸዉን በአብነት አንሥተዋል፡፡ በታየዉ ተጨባጭ ለውጥ ምክንያት ኢትዮጵያ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ኮንፈረንስን ማስተናገዷንም . ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ የተገኙ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የጥንታዊት ጀግኖች ዐርበኞች ማኅበር ኃላፊዎች፣ ምሁራንና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሰል መድረኮች እንዲሰፉ፣ ብዝኃነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን የበለጠ መገንዘብ እንዲቻል ሐሳቦችን ሰጥተዋል፡፡ ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ በሚል መሪ መልእክት እየተከበረ የሚገኘዉ የኅብር ቀን ከፓናል ውይይት በተጨማሪ በበጎ አድራጎት እና ማዕድ ማጋራት፣ በእግር ጉዞ እና በልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ሥራዎች እየተከበረ ይገኛል፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ጳጉሜን 2/2017 ዓ/ም

Similar Posts