ዛሬ የ2018 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ የጀመርነው የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት በመጎብኝት ነው።
ፕሮጀክቱ ባለፈው ከነበረኝ ጉብኝት በኋላ የሚለካ የሥራ እድገትም ታይቶበታል። የግድቡ ከፍታ 128 ሜትር የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ የሲቪል ሥራው 70 ከመቶ ደርሷል። ይኽ ስኬት ለኃይል ምንጭ ዋስትናችን ላለን ያላሰለሰ ጽኑ ጥረት ምስክር የሚሆን ነው።
Today, we begin the Council of Ministers’ macroeconomic evaluation for the first 100-days of the Ethiopian calendar year 2018 with a visit to the Koysha Hydroelectric Power Project. Since my last review, the project has shown remarkable progress, now standing 128 meters high and reaching 70% completion of civil works. This milestone stands as a testament to our continued commitment to achieving energy security.


















