በኢትዮጵያ በዲጂታል ጤናው ዘርፍ፣ በሰው ሀብት ልማት እና በጤና ፋይናንስ ማሻሻያ ስራዎች ዙሪያ ተጨባጭ ለዉጦች ተመዝግበዋል ፡፡
የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ከክልል ጤና ቢሮዎችና የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 27ኛው ዓመታዊ የጤና ሴክተር የምክክር ጉባኤ ካዘሬ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም በጅማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ጉባኤዉ በሀገር አቀፍ የጤና ግቦችና እና የማሻሻያ ክንዉኖችን፣ እንዲሁም ቀጣይ የዘርፉ አቅጣጫዎችን ለመገምገም ዓላማ ያደረገ ሲሆን፣ በተለይም በመንግስትና ባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራርን ከማጎልበት ባሻገር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጠራን ለማስፋፋት ያለመ ነው።
መንግስት በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት መጠነ ሰፊ ስራችዎችን እያከናወነ በመሆኑ ይህ ሀገር አቀፍ ጉባኤ የተገኙ ዉጤቶችን የሚያስቀጥል እና በመላ አገሪቱ ፍትሃዊ፣ እንዲሁም ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማቅረብ ጠንካራ የመንግስት ቁርጠኝነት መኖሩን የሚያጎላ ነዉ፡፡
ኢትዮጵያ በእስካሁኑ በዲጂታል ጤና፣ በሰው ሀብት ልማት እና በጤና ፋይናንስ ማሻሻያ ስራዎች ዙሪያ ተጨባጭ ለዉጦችን አሳይታለች፡፡ የምክክር ጉባኤዉ ጉባኤው ሀገራዊ የጤና እንክብካቤ ዑደትን በማጠናከር የዘርፉ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የጤና ውጤቶችን ይበልጥ ለማላቅ ተግባራዊ ተሞክሮን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡



