አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያን በተመለከተ
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለቤት ያደርገዋል። ለዚህ ግዙፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንትም ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቬሽን ማእከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል።
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለቤት ያደርገዋል። ለዚህ ግዙፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንትም ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቬሽን ማእከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል።
Office of the Prime Minister-Ethiopia
ኅብረ ብዙ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለኅብር ቀን በሰላም አደረሳችሁ! ጳጕሜን 4 የኅብር ቀን “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ መልዕክት ተከብሮ ይውላል፡፡ በእርግጥም የኅብር ቀን ኢትዮጵያውያን ዓመቱን ሙሉ ልናከብረዉ የሚገባ ነው፤ ኅብራችን ብዙ ነውና፡፡ በብሔር፣ በቋንቋ፣ በአመለካከት፣ በመልክዓ ምድር፣ በአመጋገብ፣ በአኗኗር ዘይቤ፣ በአለባበስ ወ.ዘ.ተ፡፡ ኅብራዊነታችን ሰፊ ነው፡፡ ይህ ኅብራችን ደግሞ ውበታችን፣ ሀብታችን፣ የደስታና የጥንካሬያችን ምንጭ ነው፡፡…
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 5/2017(ኢዜአ)፦ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የተመድ የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ሀገራዊ ፋይዳ በመገንዘብ የተደራጀ መረጃ ተደራሽ ሊያደርጉ እንደሚገባ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ። ኢትዮጵያ 2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥርዓተ-ምግብ ጉባኤን ከሁለት ሳምንት በኋላ ታስተናግዳለች። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት መገናኛ ብዙሃን ጉባኤውን በተመለከተ ሊኖራቸው የሚገባው ግንዛቤ እና የሥርዓተ ምግብ ሽግግር ፅንሰ…
ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማሳያ ናቸው። ብዝኃነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫዋ የኾነችው ኢትዮጵያ የክረምቱን መገባደድ የሚያበስሩ ትውፊቶች ባለቤት ናት። ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ልጃገረዶች ወደ ዐደባባይ በመውጣት የሚያሰሟቸዉ ኅብረ ዝማሬዎች በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የክረምቱን መገባደድ፤ በየጋራ ሸንተረሩ የአበቦችን መፍካት፣ የምንጮችን መጥራት እና የቡቃያዎችን ማፍራት ያበስራሉ። ከእነዚህ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች መካከል ከነሐሴ…
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 47ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ በዚህም መሰረት፦ 1. 2018 ዓ.ም የፌዴራል መንግስት በጀት በአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን ከማስፈጸም፤ የሀገር ደህንነትን ከማስጠበቅ፣ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ፣ በተፈጥሮና ሠው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ከመርዳት አንጻር፤ የ2018-2022 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍን መሠረት…
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በድምቀት ተከበረ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ታሪካዊዉ የዘንድሮ የዓድዋ ድል በዓል፣ “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሐመድ እና የቀድሞው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማትን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፤ አርበኞች፣ የመከላከያና የፀጥታ አካላት አመራሮች፣ ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች…
ዓለም አቀፍ “የመታወቅ ቀን” በመስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡ መታወቂያ ማግኘት የዜጎች መብት ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊ መብት እንደመሆኑ መሠረታዊ አገልግሎትን ለማግኘት ፥ መብትን ለማስጠበቅ እና በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ሙሉ ተሳትፎ ለማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ፣ሁሉም ሰው መታወቅ ይገባዋል፣ሁሉም ሰው የመታወቅ መብት አለው። እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 16 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ “የመታወቅ ቀን” ዘንድሮ…