ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው !

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው !

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ጥቅምት 22/02/2018

መንግሥት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት እንዲቻል የተኪ ምርት ስትራቴጂን በመቅረጽ ወደ ሥራ በመግባቱ ከፍተኛ ውጤቶች ተመዝገባዋል ።

ስትራቴጂው የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር፣ የወጪ-ገቢ ምርት እንዲመጣጠን እና ሀገራዊ ሉዓላዊነትን እንዲረጋገጥ እያደረገ ይገኛል ።

በተለይ በውስጥ አቅም መቅረብ የሚችሉ ዋና ዋና የገቢ ምርቶች ተለይተው ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርቶች እንዲተኩ ትኩረት መደረጉ የውጪ ምንዛሬ ከማዳን እና ከሥራ እድል ፈጠራ አንጻር ፋብሪካዎችን ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆኑ አድርጓል ።

የተኪ ምርት ስትራቴጂ በሁሉም ዘርፍ በተሟላ መልኩ ገቢራዊ መደረጉ ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፉ የተሻለ የሥራ ዕድል አጋጣሚ የተፈጠረ ሲሆን ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ በተለያዩ ዘርፎች በተኪ ምርት ላይ በተከናወኑ ሥራዎች 1 ነጥብ 08 ቢሊዮን የአሜርካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማዳን ተችሏል ።

በሀገራችን ነባራዊ የፍጆታ ፍላጎት አንፃር የትኞቹ ምርቶች በቅድሚያ ይተኩ በሚል በምግብ እና መጠጥ፣ በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ፣ በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ፣ ብረታብረት እና ቴክኖሎጂ ላይ በማተኮር 96 ተወዳዳሪ ተኪ ምርቶች ተለይተው በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የተደረገው ጥረት እንደሀገር ፍሬ እያፈራ ይገኛል ።

ለአብነት የጥጥ ምርትን ፍላጎት ሙሉበሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን በሚደረገው ጥረት በአፋር ክልል በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች እና አርሶአደሮች በ17ሺህ 121 ሄክታር መሬት ላይ ጥጥን እያለሙ ይገኛል ።

እንደሀገር በ2017/18 የምርት ዘመን ለጥጥ ምርት ተስማሚ በሆኑ ቆላማ አካባቢዎች ለማልማት በዕቅድ ከተያዘው 110 ሺህ ሄክታር መሬት በጥሬ ጥጥ 1.9 ሚሊዮን ኩንታል የተገኘ ሲሆን በዘንድሮው የምርት ዘመን ለኢንደስትሪዎች የሚፈለገውን ያህል የጥጥ ምርት በመጠንና በጥራት ማቅረብ ተችሏል ፡፡

የማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪዎች የግብአት ችግር እንዳይግጥማቸው ሃገር ውስጥ ያለውን እምቅ አቅም ለመጠቀም በመንግሥት ሰፊ ሥራ እየተሰራ ሲሆን በውጤቱም ተጨማሪ እሴት ያለውን የሃገር ውስጥ ምርት 60% በመቶ ለማድረስ እና የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ትኩረት ተደርጓል ።

Similar Posts