ሕዝባዊ ዉይይቶች የሰላምና ጸጥታ መሠረት ናቸዉ
ታኅሳስ 13/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ምክንያቱም ከሰላም የበለጠ ምንም ነገር የሌለ በመሆኑ፡፡ ሰላም ለሰው ልጅ እድገትም ሆነ ለሀገር ግንባታ ሂደት ዋንኛዉ መነሻ ነው፡፡
ሰሞኑን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የተደረጉ ሕዝባዊ ዉይይቶች የሕዝብ ድምጽ ጎልቶ እንዲሰማ ማድረጉንና ሕዝቡ ለዘላቂ ሰላምና ልማት ቁርጠኛ መሆኑን የታየበት ሁነኛ መድረክ ነበር፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊዎች የሀገሪቱን ሰላምና ጸጥታን፣ እንዲሁም የተያዘዉን የብልጽግና ጉዞን እዉን ለማድረግ ሀገራዊ አንድነቱን የሚሸረሽሩ አዝማሚያዎችን መከላከልና መቆጣጠር ቁልፍ ስራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በተለይም ሰላምና ጸጥታን ማስፈን የሙሉ ጊዜ ስራ በመሆኑ ሕዝቡ አካባቢዉን በንቃት መከታተል፣ መጠበቅ፣ ከመንግስት ጸጥታ ሀይሎች ጋር በቅርበት መስራት አዋጭነቱ የጎላ መሆኑን አመላክቷል፡፡
መድረኮቹ የህዝቡን ድምጽ ከማጉላት ባለፈ በዜጎችና በመንግስት ተቋማት መካከል ያለዉን ግንኙነትም እንዲጠናከር የሚያግዝ ነው፡፡ በየጊዜዉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በግልጽ በመፍታትና መፍትሄዎችን በማቅረብ የመተማመንና የትብብር ድልድይ እንዲፈጠር አስችሏል፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊዎች ለሰላም ዘብ መቆም ከሁሉም የሚጠበቅ ሀላፊነት መሆኑን በመግለጽ የእኩይ ሀይሎች ተግባራትን ለመከላከል መንግሥት ቀጣይነት ያለዉ እርምጃ እንዲወሰድም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሰላምና ጸጥታን ማስፈን የዜጎች ሙሉ ተስፋ፣ ነጻነትና ክብር መረጋገጥ ሚናዉ የጎላ ነዉ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሕዝባዊ የዉይይት ሂደቶች ለሀገራዊ አንድነትና ጽናት እያደገ የመጣዉ የመንግስት ቁርጠኝነትን ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃ
👇https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

