በ2014 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 41 የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ አንድ በመሰብሰብ የኢትዮጵያን ሃብት የማወቅ፣ ተበታትኖ የቆየውን ሃብት በተደራጀ መንገድ የማስተዳደር ስራ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል።
በ2014 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 41 የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ አንድ በመሰብሰብ የኢትዮጵያን ሃብት የማወቅ፣ ተበታትኖ የቆየውን ሃብት በተደራጀ መንገድ የማስተዳደር ስራ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል። ተቋሙ ከመመስረቱ አስቀድሞ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የፋይናንስ፣ የኦዲት፣ የካፒታል፣ የብድር ጫና እና የኮርፖሬት አስተዳደር ችግር ውስጥ የነበሩ ናቸው። አሁን ላይ በኢትዮጵያ ኢንቨትመንት ሆልዲንግስ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ዘመናዊ የባለቤትነት፣ የአስተዳደር ስርዓት እና ዓለም አቀፍ የኮርፖሬት አስተዳደር ስርዓት ተዘርግቶላቸዋል። በተጨማሪም ዘመናዊ የኦዲት ስርዓት እንዲከተሉ ተደርጓል።
ይህም ተቋማቱ ከኪሳራ ወጥተው ወደ ትርፋማነት እንዲሸጋገሩ አስችሏል። ባለፉት አራት ዓመታትም የተቋማቱ አጠቃላይ ገቢ ቀድሞ ከነበረበት ከ704 ቢሊየን ብር ወደ 6.1 ትሪሊየን ብር ማሳደግ ተችሏል። የመንግስት የልማት ድርጅቶች ዛሬ ላይ በ36 ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ። በአጠቃላይ በእነዚህ ተቋማት ስር ያለው የሃብት መጠንም 8.2 ትሪሊየን ብር ደርሷል። በዚህም የመንግስት የልማት ድርጅቶች በኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ ይበልጥ በማጠናከር ድርጅቶቹ ከኢትዮጵያ ተሻግረው በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ

