የሀገር ውስጥ የነዳጅ አቅርቦትን እንዴት ማስቀጠል ተቻለ? የኢትዮጵያ አየር መንገድስ በአለም አቀፉ የነዳጅ ቀውስ እንዴት ሥራ አላቆሙም ? ኢትዮጵያዊያን ይህንን ጥያቄ ሊጠይቁ ይገባል !!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

መንግሥት የሚከተለው የጠራና ስትራቴጂካዊ ፖሊሲ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰቱትን ፈታኝ የኢኮኖሚና የነዳጅ ቀውሶች በጽናት እንድትመክት የሚያስችል ጠንካራ ሉዓላዊ አቅም አጎናጽፏታል።

ይህ ሀገራዊ የጽናት ልዕልና በተጨባጭ የታየው እንደ ሊፍታንዛ ያሉ ግዙፍ የአውሮፓ አየር መንገዶች በነዳጅ እጥረት አቅም አንሷቸው በረራ እስከመቀነስና ሌሎች ሀገራት ደግሞ በአጭር ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ በረራ ለማቋረጥ እንደሚገደዱ ባስታወቁበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለምንም መስተጓጎል ሰማዩን መቆጣጠር መቻሉ ነው። ይህ ስኬት ድንገተኛ አጋጣሚ ሳይሆን፣ መንግሥት በጥልቀት የዘረጋው ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ ጥበቃ ፖሊሲ ያፈራው አንፀባራቂ ፍሬ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

የሀገር ውስጥ የነዳጅ አቅርቦት ቀጣይነትም ቢሆን የዚሁ የላቀ አቅጣጫ ማሳያ ነው። መንግሥት ላለው ውስን ሀብት ስልታዊ ቅደም ተከተል በመስጠት መሠረታዊ ሸቀጦች ቅድሚያ እንዲያገኙ ያደረገው የውጭ ምንዛሬ አመደበብና የታለመ የድጎማ ማሻሻያ ፖሊሲ፣ የሀገርን ኢኮኖሚ ከከፋ አደጋ ታድጓል።

ከዚህም ባሻገር፣ የነዳጅ ጥገኝነትን በዘላቂነት ለመስበር ተግባራዊ የተደረገው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፈጣን ሽግግር ሀገራዊ የማክሮ-ኢኮኖሚ ጫናውን በከፍተኛ ደረጃ አቃልሎታል።

ከእነዚህ የፖሊሲ ስኬቶች በተጓዳኝ፣ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ መጎልበት እንዲሁም የዲፕሎማሲ አቅሟና ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነቷ ወደ ላቀ ደረጃ መሸጋገሩ፣ ሀገሪቱ በፈታኝ ጊዜያት አስተማማኝ የነዳጅ አቅርቦት አማራጮችን እንድታስጠብቅና ዜጎቿን ከከፋ ስጋት እንድትታደግ ሰፊ ጂኦ-ፖለቲካዊ አቅም ፈጥሮላታል።

ባጠቃላይ እነዚህ በጥልቀት የተቀናጁ የፖሊሲ እርምጃዎች፣ እያደገ ከመጣው ሀገራዊ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ስኬኮ ጋር ተሰናስለው፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መናወጦች ሳትበገር የብልጽግና ጉዞዋንና ብሄራዊ ጥቅሟን በጽናት እንድታስከብር ያስቻሏት የማይናወጡ ስልታዊ መሠረቶቿ ሆነዋል ።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts