የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን “ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻን ጎብኝቻለው።
ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው።
በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው “ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ ነው። በ38 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልም ፈጥሯል።
በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጌጋዋት ዓመታዊ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሃገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ አቅም ፈጥሯል።
በተጨማሪም በኢንደስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን ተመልክቻለው።”
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication














