ከለውጡ በፊት የሚዲያ ተቋማት ዘርፈ ብዙ ስብራቶች ነበሩባቸው፤

ሀይማኖት ዘለቀ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር እንደተናገሩት ከለውጡ በፊት የሚዲያ ተቋማት ዘርፈ ብዙ ስብራቶች ነበሩባቸው፤ ከነዚህም ጥቂቶቹ የፖሊሲ እና የማዕቀፍ ፣ የመዋቅር አደረጃጀት፣ ተቋማዊና የትክክለኛ ሙያዊ ስነ-ምግባር ስብራቶች ይገኙበታል።

‎የለውጡ መንግስት እንዚህን ስብራቶች ለማከም ጥልቅ የሆነ የሚዲያ ሪፎርሞችን አድርጓል። ሪፎርሙ ካሳካቸው ለውጦች መካከል፤ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነ የመገናኛ ብዙሃን ባልስልጣን ማቋቋም፣ የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በእርስ ቁጥጥር ስርዓት መፍጠር፣ እንዲሁም ዘርፉ እራሱን በራሱ እንዲቆጣጠር የሚያስችሉ የሙያ ማህበራትን ማበራከት ዋነኞቹ ናቸው።

እነዚህ ሪፎርሞች ትክክለኛ ውሳኔዎች ስለመሆናቸው በሚከተሉት አሃዛዊ ስኬቶች ታጅቧል፤

‎- የመገናኛ ብዙሃን ቁጥር ከለውጡ በፊት ከነበሩበት 122 ወደ 310 ከፍ ብሏል።

‎- የሬድዮ ጣቢያዎች ከለውጡ በፊት ከነበሩበት 52 ወደ 126፤

‎- የቴለቪዥን ጣቢያዎች ከለውጡ በፊት ከነበሩበት 25 ወደ 128፤

‎- የመገናኛ ብዙሀን የቋንቋ ተደራሽነት ከለውጡ በፊት ከነበሩበት 39 ወደ 60፤

‎- 35 የውጭ ሚዲያዎችና 50 የማህበረሰብ ሚዲያዎች የኢትዮጵያ የሚዲያ ምህዳር አካታችነትን በመፍጠር ላስመዘገበው ስኬት አይነተኛ ማሳያዎች ናቸው።

#PMOEthiopia

See less

Similar Posts