የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“ታላቅ ወንድሜ እና ውድ ወዳጄ ክቡር ናሬንድራ ሞዲ፣ የዓለማችንን ትልቁን እና እጅግ ንቁ የሆነውን የዲሞክራሲ ማህበረሰብ ዘላቂ እምነት በማግኘት፣ ህንድን በራዕይ እና በቁርጠኝነት በተከታታይ ሶስት የዲሞክራሲያዊ የስልጣን ዘመናት በመምራት ላስመዘገቡት ታሪካዊ ስኬት የተሰማኝን ደስታ እገልጻለሁ።
የእርሳቸው አመራር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከድህነት ያወጣ፣ የዲጂታል ሕዝባዊ መሰረተ ልማትን በከፍተኛ ደረጃ ያስፋፋ እና ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ የመሰረተ ልማት እድገትን በማምጣት ፈጣን የኢኮኖሚ መነቃቃትን ያስገኘ ነው። በተጨማሪም በተከታታይነት ለደቡቡ የዓለም ክፍል (Global South) ጠንካራ ድምጽ በመሆን አገልግለዋል።”
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication



