የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ክቡር ወርቅነህ ገበየሁ በሀገራዊ ምክክር መክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልእክት

ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዓለም ታሪክ ውስጥ በግጭት የተገነባ ወይም ያተረፈ ሀገር አለመኖሩን አስገንዝበዋል። አክለውም በፖለቲካ ባህል ውስጥ ልዩነቶች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ቢሆንም፤ ትልቁና መሰረታዊው ስህተት ግን እነዚህን ልዩነቶች በኃይል ለመፍታት መሞከር እንደሆነ ነው ያነሱት። ከሁሉ በላይ ልዩነቶችን መፍታት የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ፣ በመነጋገርና በተለያዩ ሰላማዊ መድረኮች መሆኑን ያብራሩት ዋና ፀሐፊው፤ ኢትዮጵያም ለዚህ የሚሆኑ በርካታ ባህላዊ የምክክር መንገዶች ያሏት ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል።

PMOEthiopia

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts