ኢትዮጵያ እየተከለች ነዉ።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ (ዶ.ር) በአንድ ጀንበር #600_ሚሊየን_ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ላይ አሻራቸዉን አሳረፉ።


በሕዝብ ግፊትና በፓርቲ ሳቢነት የመጣው ሀገራዊ ለውጥ፣ የመጀመሪያውን ምእራፍ እየተሻገረ ነው፡፡ በዚህ የመጀመሪያ ምእራፍ የለውጡን ሐሳቦች በቃልና በተግባር ተገልጠዋል፡፡ የለውጡ ፈተናዎችም አካል ገዝተው በሚገባ በመገለጣቸው ሕዝብ ዐውቆ እንዲታገላቸው ተደርጓል፡፡ ይሄም የለውጡን ፍሬዎች ለማጎምራት፣ የለውጡን ፈተናዎችንም ለመርታት ዕድል ሰጥቷል፡፡ ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ሲጠየቁ የነበሩ ጥያቄዎች ከቃል አልፈው ተግባራዊ ምላሽ አግኝተዋል፡፡ የፖሊሲ፣ የሕግ…
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ፈጣን የሽግግር ለውጥ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራበት ይገኛል፡፡ በተለይ በሳይበር ጥቃቶች ላይ የመቋቋም አቅምን፣ የአቅም ግንባታን፣ ጠንካራ የህግ ማዕቀፎችን እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ትኩረት ተደርጓል፡፡ ስትራቴጂው ከአገር አቀፍ የልማት ግቦች ጋር የሚጣጣም፣ በሳይበር መረብ ላይ እምነትን ከማሳደጉም ባሻገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣…
ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ የቀድሞ ፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ መሪዎች ቤተሰቦች እና ጋዜጠኞች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት በሰጡት አስተያየትም “ኢትዮጵያ ፓን አፍሪካኒዝምን በላቀ መሠረት ላይ ገንብታዋለች፤ ይህ ለአፍሪካ ሌላ ዐዲስ ምዕራፍ ነው” ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያውያን በራስ ዐቅም እና ጥረት የተገነባዉ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከዓድዋ ድል እና ከአፍሪካ ኅብረት ምሥረታ ቀጥሎ ሦስተኛዉ የፓን አፍሪካኒዝም መሠረት…
*************************************** የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በ2017 ዓ.ም ኢትዮጵያ ታላላቂ የታሪክ እጥፋቶችን ያሳየችበት ስኬታማ እንደነበር በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ብዝኃ ዘርፍን መሠረት አድርጎ የተነደፈዉ ፖሊሲ ኢትዮጵያን ወደላቀ ብልጽግና እያሸጋገረ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣…
የ2018 ሀገራዊ የልማት አቅድ በሁሉም ዘርፎች የተገኙ እምርታዊ ዉጤቶችን የሚያስቀጥልና ለላቀ ዉጤት የተደመረ አቅም የሚፈጥር እቅድ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የአገልግሎቱ አመራርና ሰራተኞችም በእቅዱ ላይ ዛሬ ዉይይት አድርገዋል፡፡ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ሀገራዊ እቅዱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም በሁሉም ዘርፎች ያስመዘገበችዉ የኢኮኖሚ እድገት እምርታ የታየበት መሆኑን…
ንግድን ለማቀላጠፍና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለመደገፍ የመንገድ አውታሯን በንቃት እያስፋፋችና እያሻሻለች ትገኛለች። አሁን ላይ እየተከናወኑ ያሉ ጥረቶች ትኩረት የሚያደርጉት አዳዲስ አውራ ጎዳናዎችን እንዲሁም የገጠር እና የከተማ መንገዶችን በመገንባት በተጨማሪም ነባር መንገዶችን በማዘመን የጉዞ ጊዜን ለማሰጠር፣ ደህንነትን ለማሻሻልና የትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስ ነው። እነዚህ ተግባራት የትምህርት፣ የጤና፣ የገበያ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ከማሳደጋቸውም በላይ ለኢንዱስትሪ፣ ለግብርና እና…