ሀሳብ የለውጥ ኃይል ነው ምሁራን ደግሞ የለውጥ ወኪሎች ናቸው።”-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምሁራን በማህበረሰብ ውስጥ የሚፈጥሩት ለውጥ ሀገርን ወደ ብልጽግና እንደሚያሸጋግር በመጥቀስ ምሁራን የለውጥ ወኪልና የሀሳብ ኃይል መሆን እንደሚገባቸው አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት በማስመልከት በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው። በመድረኩ ላይ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ምሁራን በሁለንተናዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሚና በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው ምሁራን ሊላበሷቸው የሚገቡ እሴቶችን ሲገልፁ “ምሁራን የሀሳብ አፍቃሪ፣ ጥልቅ አሰላሳይ፣ አንባቢ፣ እንዲሁም ችግር ፈቺና መፍትሄ አሳሽ መሆን ይጠበቅባቸዋል” ብለዋል። በተጨማሪም “የመደመር” መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ በመግለጽ፣ ተቋማቱ በሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ ያላቸውን ድርሻ አይተኬ መሆኑን መንግስታቸው በጽኑ እንደሚያምንጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማርና የምርምር ተግባራቸውን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማናበብ ወደ ፈጠራና ተግባር መለወጥ እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ይህም የኢትዮጵያን ብልጽግና በተደመረ አቅም ለማፋጠን የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፅንኦት ተናግረዋል ፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts