በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ሙዚየም የተደረገ ጥልቅ የታሪክ ጉዞ!

‎የሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አካል የሆነውን የብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ሙዚየምን ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ የኢትዮጵያን ነፃና ጥንታዊ ሥልጣኔ የሚያሳይ ሲሆን፤ የሀገሪቱ ታሪክና ቅርሶችም ለታማኝና ባለርዕይ አጋርነቷ ህያው ምስክሮች ሆነዋል። ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት መሆኗን የሚያሳዩ ታሪካዊ ቅርሶቿን ስታጋራ፣ ጥንታዊ ጥንካሬዋ ለዘመናዊውና ለውጥን ለሚያረጋግጠው አጋርነቷ መሠረት መሆኑን በድጋሚ እያረጋገጠች፤ አፍሪካውያን ወንድሞቻችንን ለጋራ የወደፊት ዕጣ-ፈንታ በአንድነት ለመሥራት ወደ ሁለተኛ ቤታቸው እንዲመጡ ጥሪ የምታቀርብበት ነው።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts