በኢትዮጵያ እና በሩስያ መካከል ለረጅም ዓመታት የዘለቀውን የታሪክ፣ የባህልና የዲፕሎማሲ ትስስር በአግባቡ የሚያንፀባርቅ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚገባ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ ተናገሩ።

በኢትዮጵያ እና በሩስያ መካከል ለረጅም ዓመታት የዘለቀውን የታሪክ፣ የባህልና የዲፕሎማሲ ትስስር በአግባቡ የሚያንፀባርቅ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚገባ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ ተናገሩ።


በሩሲያዋ ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ከሚካሄደው የአፍሪካ ሩሲያ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ሚኒስትር ዲኤታዋ ከሩስያ የዲጅታል ልማት፣ ኮሙኒኬሽንና ማስ ሚዲያ ምክትል ሚኒስትር ቤላ ቼርኬሶቫ ጋር ውይይት አካሂደዋል።
በውይይታቸውም አፍሪካውያን የዓለም አቀፍ የሚዲያ አማራጮቻቸውን ለማስፋት እንዲችሉ በሩሲያ የሚገኙት ትልልቅ መገናኛ ብዙሃን የአቅም ግንባታ ስራዎችን መስራት እንደሚገባቸው አንስተዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ሃሰተኛ መረጃዎች፣ የጥላቻ ንግግር እና ተመሳሳይ ችግሮች እያመጡ ያሉትን ጉዳት ለመቀነስ ሁለቱ ሃገራት ልምድ ለመለዋወጥና ውጤታማ የሆኑ አሰራሮችንም ለመተግበር ተስማምተዋል፡፡
የመንግስት አጀንዳዎችን ለሁሉም ዜጎች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ወሳኝ መሆኑን በማንሳት ለኢትዮጵያ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ስልጠናና የትምህርት እድሎችን ሩስያ ለመስጠት ፍላጎት እንዳላት ምክትል ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ እየሰራች ነው ያሉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታዋ ሰላማዊት ካሳ ይህንንና ሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ ሚዲያው ትልቅ ሚና አለው ብለዋል። የሁለቱ ሃገራት የሚዲያ ሥራም የሃገራቱን ግንኙነት ወደሚመጥን ደረጃ ከፍ ማለት እንዳለበት እንዲሁም ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መናኽሪያ በመሆንዋ የሩስያ ሚዲያዎች በአዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ ሚዲያዎችም በሩስያ ቢሮ እንዲከፍቱ ለማገዝ ተስማምተዋል።

Similar Posts