በ3ዲ ህትመት፣ በቅድመ-ዝግጅት ብረት እና በኮንቴይነር ግንባታ የሀገሪቱን የቤት ልማት ለማቀናጠፍ የተጀመረው ተስፋ ሰጪ ጉዞ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባችንን ተከትሎ፣ እጅግ ዘመናዊና ፈጣን የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም የተገነቡ ቤቶችን የሚያሳይ የግንባታ ሳይት ጎብኝተናል። በዚህ ሳይት ሦስት የላቁ የግንባታ ዘዴዎች በጥምረት ጥቅም ላይ ውለዋል፤ የ3ዲ ህትመት(3D printing)፣ የቅድመ-ዝግጅት ቀላል የአረብ ብረት ግንባታ እና የኮንቴይነር መኖሪያ ቤቶች ናቸው። እያንዳንዳቸው ግንባታዎች ትክክለኛውን ቴክኖሎጂ ስንጠቀም ፍጥነት እና ጥራት እርስ በእርስ የማይጋጩ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፤ ጥራታቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ከወራትና ከዓመታት ይልቅ በጥቂት ቀናት እና ሳምንታት ውስጥ ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል የታየበት ህያው ምስክር ናቸው።

‎ይህ አይነቱ የላቀ ፈጠራ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በቀላሉ ሊተገበር፣ ሊደገም እና ሊስፋፋ የሚችል በመሆኑ የሀገራችንን የቤት ልማት ፕሮግራም አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ የመቀየር ኃይል አለው። ቴክኖሎጂን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር አጣምረናል፤ መሰል በተግባር የተገለጡ ስራዎቻችን ደግሞ ለሀገር የሚገባውን ፈጣን እድገት እውን ለማድረግ በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ በቁርጠኝነት እየተጓዝን መሆናችንን በተግባር አሳይቷል!

Similar Posts