ባለፉት የለውጥ ዓመታት በገቢዎች ዘርፍ ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም የማሳደግ
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በገቢዎች ዘርፍ ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም የማሳደግ፣ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓት የመገንባት፣ የታክስ ህግ ተገዢነትት የማረጋገጥ እና ዘላቂ የገቢ እድገትን የማረጋገጥ ስራዎች ተከናውነዋል።
ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተገናኘ ዘመናዊ የግብር ስርዓትን ለመዘርጋት ተሰርቷል። በ2011 በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ታክስ በማሳወቅ ረገድ 10.1 % በመቶ ብቻ የነበረው አሰራር በ2017 ዓ.ም 94 በመቶ የሚሆኑ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በኢ-ፋይል አሳውቀዋል። በተመሳሳይ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ግብር የከፈሉ የግብር ከፋዮች በ2011 ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ በ2017 ወደ 64 በመቶ ማሳደግ ተችሏል። ዘመናዊ የግብር ስርዓትን በማጠናከር ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና የታክስ ተደራሽነትን ለማስፋት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
በ2018 ባለፉት ስድስት ወራት 709 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል። ይህ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ256 ቢሊየን ብር ብልጫ ያለው ነው። በ2018 በጠቅላላው 2 ነጥብ 1 ትሪሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል። በቀጣይም ቴክኖሎጂ መር የታክስ አስተዳደርን የበለጠ በመዘርጋት የታክስ ስወራን መከላከል፣ በግብር ከፋዩ እና በታክስ አስተዳደሩ መካከል መተማመን ላይ የተመሰረተ የታክስ ስርዓትን ለመከተል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
- ወ/ር አይናለም ንጉሴ
የገቢዎች ሚኒስትር
PMOEthiopia
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

