ባለፉት የሪፎርም ዓመታት የገንዘብ ፖሊሲን የማዘመን

ባለፉት የሪፎርም ዓመታት የገንዘብ ፖሊሲን የማዘመን፣ የውጭ ምንዛሬ የማሻሻል ፣የፋይናንስ ዘርፍ ለውጥ እና የተቋማዊ ማሻሻያ ስራዎች ከተከናወኑ ዋና ዋና የማሻሻያ ተግባራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

እነዚህ የማሻሻያ ተግባራት የዋጋ ግሽበትን በሰኔ 2012 ከነበረበት ከ30 በመቶ በታህሳስ 2018 ላይ ወደ 9.7 በመቶ ለመቀነስ አስችለዋል።

በውጭ ምንዛሬ ማሻሻያ ትግበራ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከማሳደግ ባለፈ በህጋዊ እና ትይዩ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ተችሏል።

አሁን ላይ ለግሉ ዘርፍ የሚቀርብ የብድር ድርሻ 77% ደርሷል። ዲጂታል አካውንቶችን በተመለከተም 254 ሚሊዮን አካውንቶች ማድረስ ያስቻለ ማሻሻያ ነው።

‎በቀጣይ የዋጋ ንረትን በነጠላ አሃዝ እንዲቆይ ማድረግ፣ የውጭ ምንዛሬ ገበያውን የበለጠ ተገማች እና የተረጋጋ ማድረግ፣የባንኮች ውህደት እና ግዢ ተግባራዊ ማድረግ፣ የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚመራ ተቋምን ማደራጀት፣ የወለድ ነጻ የባንኪንግ ስርዓትን ማጠናከር ትኩረት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው።

  • ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
    ‎የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ

PMOEthiopia

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts