አምራች ኢንዱስትሪው ከኢኮኖሚ ነፃነት እስከ ሉዓላዊነት ልብ !

“እኔ አምራች ኢንዱስትሪን የሀገራችን ‘የሉዓላዊነት ልብ’ አድርጌ ነው የምመለከተው ምክንያቱም አንዲት ሀገር በምግብ፣ በልብስና በመሰረታዊ ፍላጎቶቿ በሌሎች ላይ ተንጠልጥላ የምታወራው ሉዓላዊነት ሙሉ ሊሆን አይችልም። ላለፉት ዓመታት በንግድና በአገልግሎት ዘርፍ ላይ ብቻ ተንጠልጥለን መቆየታችን ስህተት እንደነበር በመገንዘብ፣ አሁን የጀመርነው ‘ኢትዮጵያ ታምርት’ ንቅናቄ ሀገራችን በራሷ አቅም ፍላጎቶቿን እንድታሟላና እውነተኛ የኢኮኖሚ ነፃነቷን እንድታረጋግጥ ታስቦ የተነደፈ ነው።

ይህ የኢንዱስትሪ ዘርፍ በሁለት መንገዶች የኢኮኖሚያችን አከርካሪ ይሆናል ፤ አንደኛው የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን የምናድንበት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለዓለም ገበያ በማቅረብ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ የምናስገኝበት ነው። ይህ ሂደት አሁን ካለነው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተዳምሮ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ሰፊ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር የምናመጣበት ትልቅ ‘ትምህርት ቤት’ ነው። በዚህም ወጣቱ ትውልድ በዘመናዊ አሰራርና በፈጠራ የታገዘ የሥራ ባሕል እንዲኖረው በማድረግ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርታችንን ከኢንዱስትሪው ፍላጎት ጋር በማጣጣም የሥራ አጥነትን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራን እንገኛለን።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts