አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያን በተመለከተ
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለቤት ያደርገዋል። ለዚህ ግዙፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንትም ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቬሽን ማእከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል።
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለቤት ያደርገዋል። ለዚህ ግዙፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንትም ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቬሽን ማእከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል።
Office of the Prime Minister-Ethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ጥበቃ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን ጨምሮ ሰፊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ውይይቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁህ ኃይል ምንጭ የሚውል የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ የማልማት ስምምነቶችን ጨምሮ የጋራ ፍላጎት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተካሂዷል። Prime Minister Abiy Ahmed held talks with President Vladimir Putin on a…
“ኢትዮጵያ ለሁለንተናዊ ጉዳዮች ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ትገኛለች። በሚዲያ ሥራ ጥረቶቻችን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሰላም እና ፍቅር ቅድሚያ ሰጥተን መሥራት ይገባናል። ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር ምን ጠቃሚ ሥራ እየሠራን ነው ብለን ራሳችንን ሳናሰልስ መጠየቅ አለብን። በዛሬው ዕለት ሀገራዊ ልማት እና ኅብረትን በማስተዋወቅ ብሎም ብሔራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ ጥረት ረገድ ከፍ ያለ ሥራ በመሥራት ሽልማት ለተበረከተላቸው የሚዲያ ተቋማት…
ዛሬ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ትዕይንቶች ተደርገዋል። ሕዝቡ በዚህ ትዕይንተ ሕዝብ ላይ ለሰላም ያለውን አቋም በድጋሚ ገልጿል። ፀረ ሰላምና ተላላኪ ኃይሎች በሚፈጽሙበት ግፍ ተማሯል። በደሙና በላቡ የገነባቸው መሠረተ ልማቶች ‘የአንተ ነን’ በሚሉት የጠላት ተላላኪዎች ሲፈርሱበት በአይኑ አይቷል። ልጆቹ ከትምህርት፣ ከብቶቹ ከግጦሽ እየተከለከሉ እጅ ከወርች ታስሮ ከርሟል። በዚህ የተነሣ ተላላኪዎቹን ጽንፈኞች ለመታገል ቆርጦ የተነሳው ሕዝብ…
ከክረምቱ ዝናብ ጋር ተያይዞ በአንድ አንድ የሃገራችን አካባቢዎች በደረሱ የመሬት መንሸራተትና የዉሃ ሙሌት ምክንያት የበርካታ ዜጎቻችን ሕይወት አልፏል፤ የአካል ጉዳትና የንብረት መውደም አደጋም ደርሷል፡፡በትናንትናው ምሽት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ ግሽሬ ጉዱ ሞና ሆሞ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 (ስድስት) ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ የአካል…
ሰላማዊ ካሳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሕብረ ብሄራዊነት የተከበረባት ጠንካራ አንድነት ያላት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ታላቁን ገዥ ትርክት በጋራ ልንገነባ ይገባል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊ ካሳ ተናገሩ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ዛሬ በጀመሩት ውይይት ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳሉት እንደ መንግስት ኮሙኒኬሽን አመራርና ባለሙያ ለሃገራዊ ግንባታ አዎንታዊ ገዥ…
ምክር ቤቱ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች፡- 1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ነው፡፡ ኮሚሽኑ ሀገራችን የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ መንገድ ከዓለም አቀፍ ማዕቀፎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በምግብ ዋስትና፣ በጤና አገልግሎት፣ በሳይንስ እና ምርምር ዘርፎች ላይ ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት የመምራትና…