ኢትዮጵያዊያን ለሰላም፣ ለልማትና ዲሞክራሲ በአንድነት የሚነሱበት ትክክለኛ የከፍታ ጊዜ አሁን ነዉ – የሕንድ ሪፓብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ

ታኅሳስ 8/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያዊያን ለሰላም፣ ለልማትና ዲሞክራሲ በአንድነት የሚነሱበት ትክክለኛ የከፍታ ጊዜ አሁን ነዉ – የሕንድ ሪፓብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ

ታኅሳስ 8/2018 ዓ.ም

የሕንድ ሪብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባደረጉት ንግግር፣ ጊዜዉ ትክክለኛ የኢትዮጵያ ከፍታ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለሰላም፣ ለልማትና ዲሞክራሲ በአንድነት የሚነሱበት ጊዜ አሁን ነዉ ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ኩራት እና ተስፋን በንግግራቸው አጉልተው አሳይተዋል፡

የኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ፣ አንድነት፣ ጽናት እና የሥልጣኔ መሰረት ለመላዉ አፍሪካዊያን ኩራት መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አሁን ለኢትዮጵያዊያን ትክክለኛ የከፍታ ጊዜ ነዉ በማለት በአፍሪካ እና በዓለም ላይ ላላት ተምሳሌታዊ ጥንካሬ ጥልቅ አድናቆታቸዉን ገልጸዋል፡፡

በጥንታዊቷና ጠንካራዋ ሀገር፣ ኢትዮጵያ መገኘት እድለኛ መሆን ነዉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ፣ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በህዝቦቿ ጥንካሬ፣ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ቀንዲል በመሆን የምትታወቅ ታላቅ ሀገር መሆኗን አብራርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በሕንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የጋራ እሴቶች በተለይም ስር የሰደዱ ስልጣኔዎቻቸው እና በዜጎች ላይ ያተኮሩ የልማት ፍልስፍናዎቻቸው ለደቡብ-ደቡብ ትብብር በጋራ እንዲቀናጁና በትብብር እንዲሰሩ የሚያደርጋቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራና ሌሎች የልማት መርሃ ግብሮች ያስመዘገበችዉን ውጤት አድንቀዉ ሕንድም ተፈጥሮን የመጠበቅ አቋሟ የፀና በመሆኑ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራት ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

ሕንድ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አንድነት ቁርጠኛ መሆኗን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በንግድ፣ በአቅም ግንባታ፣ በጤና እና በትምህርት እያደገ መምጣቱና ይህንንም ያስቻለ ጠንካራ የህዝብ-ለህዝብ ትስስር በመኖሩ መሆኑን በማውሳት ትስስሩን የበለጠ ለማጠናከር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሕንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈጉባዔዎችን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ታድመዋል።

ተጨማሪ መረጃ

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts