ኢትዮጵያ ለአፍሪካዊያን ያላትን አብሮነት የምታጸናበት ታሪካዊ መድረክ

ኢትዮጵያ በአህጉራዊ የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ እና በዲፕሎማሲያዊ ሚናዋ አፍሪካ የአንድነት ድምፅ እንዲኖራት እያደረገች ያለችው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ በመግለጫቸው እንዳመለከቱት፣ ሀገራችን በሰላም ማስከበር ስምሪቶች ቀዳሚ ተሳትፎ በማድረግ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነትን በፍጥነት በማጽደቅ እና ለተለያዩ አህጉራዊ ተቋማት የመሠረተ ልማት ድጋፍ በማቅረብ ረገድ ያላትን ትልቅ አሻራ በተግባር እያሳየች ትገኛለች።

አቶ ተስፋሁን አክለውም፣ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ ጉባኤ ማዘጋጀት ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲያዊ ስኬት ማሳያ ብቻ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ይልቁንም አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ኢትዮጵያ በፈተና ወቅት ላሳዩዋት አብሮነትና ወዳጅነት ምስጋና የምንገልጽበት እንዲሁም አፍሪካዊ አንድነታችንን የምናጸናበት ቋሚ መድረክ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts